ባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በ 2011 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ዉይይት አካሄደ

ከመጋቢት 12 እስከ መጋቢት 13/2011 ዓ.ም የተካሄደዉ ዉይይት በመጀመርያው ቀን የጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በየፋኩሊቲዉ  የቀረበዉን የመጀመሪያዉን  መንፈቅ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ከፋኩሊቲው ዲኖች በማዳመጥ ጀምሮ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ዉይይት በማድረግ ሲያጠናቅቅ ከሰዓት በኋላ  በነበረዉ መርሃ-ግብር ደግሞ የቸር ተጠሪዎች (chair holders)  በስራቸዉ ላሉ አባላት የግማሽ ዓመቱን እቅድ አፈፃፀም  አቅርበው በጋራ ግምገማ ተካሂዶበታል፡፡

በማግስቱ መጋቢት 13/2011 ዓ.ም የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ እቅድ ክንውን ሪፖርት በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በዶ/ር ፍሬዉ ተገኝ የቀረበ ሲሆን በተከታይም የባህርዳር  ቴክኖሎጅ ኢንስትቲዩት ግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀም በተቋሙ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር በዶ/ር ሰይፉ አድማሱ  ቀርቦ ዉይይት ተካሂዷል፡፡ ውይይቱ በዕቅድ አፈፃፀም እና በአጠቃላይ ተቋማዊ ይዘቱ ላይ የታዩትን ጠንካራና ደካማ ጎኖች የዳሰሰ ሲሆን ከታዳሚው በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ውይይት በማካሄድና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን በየደረጃው  በቀረቡ መድረኮች ላይ በመተለም ተጠናቋል፡፡

images: 
Share