ባህርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት እቅድ አፀደቀ

የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2012ዓ/ም እቅድ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ከ 24/12/2011 እስከ 25/12/2011 በጃካራንዳ ሆቴል እቅድ አቀረበ፡፡ በፕሮግራሙ ሁሉም የስራ ክፍሎች እቅዳቸዉን ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡት እቅዶች ላይ ሰፋ ያለ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ በቀረቡት እቅዶች ላይ የተሰነዘሩትን ምክረ ሀሳቦች ተካተዉ ወደ ተግባር እነዲገባ አሳስበዋል፡፡

images: 
Share