Innovator Instructors Received an Award

Three BiT staffs have received the 6th National Research and Innovation Award on a ceremony held at African Union Head Quarter, Addis Ababa at 14 Nov, 2015.

Mr. Kaledawit Esmelealem, Mr Marye Mengistu, and  Mr Muluadam Temesgen from Bahir Dar Institute of Technology (BiT), Faculty of Computing have got the official recognition from the Ministry of Science and Technology for their innovative projects. On the occasion Mr.Kaledawit Esmelealem has been awarded gold medal, and Mr. Muluadam Temesigen & Mr. Marye Mengistu have got silver medal from the hands of HE. Mr Hailemariam Desalegn, the Prime Minister of FDRE. 

The BiT Scientific Director forwards his congratulations message to the instructors for this great notational award.

Congratulations!

 

 ሀ.  በቃለዳዊት እስመላለም የተሰራው በፀሐይ እና በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ዲጅታል የትራፊክ መብራትና መቆጣጠሪያ 

ይህ በፀሐይ እና በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ዲጅታል የትራፊክ መብራትና መቆጣጠሪያ ግኝት(invention)በመኪና መንገዶች ፣ በእግረኛ ቦታዎች ፣ በባቡር ጣቢያ ፣ በኤርፖርት ጣቢያዎች እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች ላይ የተሸከርካሪን እና የእግረኛን እንቅስቃሴ የሚያቀላጥፍ መሳሪያ ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዩጵያ ለተያያዘችው የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ግንባታ ይህ ቴክኖሎጅ በመትከል የትራፊክ አደጋን የሚቀንስ፣ መንገዶች የትራፊክ መጨናነቅ ገጥሞአቸው ተሎ እንዳያረጁ የሚቆጣጠር፣ የአሽከርካሪውን ጊዜ የሚቆጥብ፣ እግረኞች በሰለጠነ መልኩ መንገዶችን እንዲያቋርጡና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ የሚያስችል ሲሆን፣ ቴክሎጅው ኢትዮጵያ ለተያያዘችው የኢንዱስትሪ ለውጥ ዋና መሳሪያ ሲሆን ዋና መቆጣጠሪያውም ኢንዱስትሪን አውቶሜት ለማድረግ የሚያስችል የፈጠራ ግኝት ነው፡፡ 

ለ. በሙሉአዳም ተመስገንና በማርየ መንገስቱ የተሰራው የተቀናጀ የገበያ መረጃ ማዕከል(Integrated Market Information System) 

1. የፈጠራ ስራዉ መነሻ ሀሳቦች፡ አርሶ አደሮች አመቱን ሙሉ በማሳቸዉ ላይ አሳልፈዉ ካመረቱት ምርት ማግኘት ያለባችዉን ጥቅም አለማግኘታቸዉ፣ ለዚህ ደግሞ ትልቁ መነሻ ራስ ወዳድ  ደላሎች ዋጋቸዉን በማራከስና በዝቅተኛ ዋጋ ስለሚገዙአቸዉ ነዉ፡ ለምሳሌ 1. በደ/ወሎ ዞን አትክልትና ፍራፍሬ በብዛት ይመረታል፡፡ አንድ ደላላ አርሶ አደሩን ከማሳዉ  ካሮት እንዲነቅልለትና በኪሎ 3.00 ብር እንደሚገዛዉ ተስማምተዉ ሃያ አንድ (21)ግመል ካሮት ጭኖ ሲሄድ ደላላዉ ሀሳቡን በመቀየር አዲስ አበባ ካሮት ስለረከሰ በኪሎ 1.50 ብር ካልሆነ አልገዛህም ይለዋል፤ አርሶ አደሩም ምንም አይነት አማራጭ ሰለአልነበረዉ ምርቱም ከማሳዉ ቀድሞ ስለተነቀለና ስለሚበላሽበት  አንድ ኪሎ በ1.50 ብር ለመሸጥ ተገዶአል፡፡. ይህ አርሶ አደር የገበያ መረጃ አማራጭ ቢኖረዉና የአዲስ አበባን የገበያ ዋጋ ቀድሞ ማወቅ ቢችል ኖሮ የተሻለ የመደራደር አቅም ይኖረዉ ነበር፤ ነጋዴዉም በድፍረት ለማጨበርበር ባልሞከረ ነበር፡፡

2. የፈጠራ ስራዉ ዉጤት: አርሶ አደሩ የቋንቋ፣ የቴክኖሎጂ፣ እና የትምህርት ደረጃ ሳይገድበዉ በአፍ መፍቻ ቋንቋዉ ባለበት ቦታ ሁኖ በቀን 24 ሰዓት ትኩስ የገበያ መረጃ ማግኘት ያስችለዋል፡፡ በዚህም የተሻለ የገበያ ትስስር በመፍጠር አርሶ አደሩ የተሸለ ተጠቃሚ በማድረግ ተጠቃሚዎች ላይ የሚፈጠረዉን የዋጋ ጫና ይቀንሳል፤ መንግስትም ገበያዉን ለማረጋጋት የሚያደርገዉን ሚና በእጂጉ ያግዛል፡፡

3. የፈጠራ ስራዉ ፋይዳ፡

 አርሶ አደሩን ካመረተዉ ምርት የተሻለ ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

 እንዲሁም በከተማ አካባቢ ያሉ ነጋዴዎች  ያላግባብ ለመክበር ለመበልፀግ ህገ-ወጥ የሆኑ ተግባራትን ሲያከናዉኑ ማህበረሰቡ በቀን ለ24 ሰዓት በድምፅ ወይም በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ጥቆማ  በማስቀመጥ ህገ-ወጥ የንግድ ስርዓትን እንዲከላከል እና መብቱን እንዲያስከብር ይረዳዋል፡፡ 

 የገበያ ትስሰር ይፈጥራል፡፡

 ግልፅ የሆነ የግብይት ስርዓት ይፈጥራል፡፡

 አዳዲስ ቴክኖሎጂን ለአርሶ አደሩ ከማስተዋወቅ አኳያ የራሱን አስተዋፅዖ ያደርጋል፡፡

 ማህበረሰቡ ለመረጃ ያለዉን አመለካካት ክፍ ያደርጋል፡፡

 በተጠቃሚዎች ላይ የሚፈጠረዉን የዋጋ ንረት ይቀንሳል፡፡

 የገበያ መረጃን ለተጠቃሚዎች እንደየፍላጎታቸዉ ከመስጠቱ በተጨማሪ የገበያ መረጃን በሞባይል ሶፍትዌር አማካኝነት በመሰብሰብ የመረጃዉን ቶሎ ወደ ተጠቃሚዎች የመድረስ ፍጥነት ይጨምራል፤ ወጭንም ይቀንሳል፡፡

4. የፈጠራ ስራዉ ስርጭት:

 የኢትዮ-ቴሌኮም አገልግሎት በደረሰበት ቦታ ሁሉ በድምፅና በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መረጃ መግኘት ያስችላል፡፡ ይህም በአሁኑ ሰዓት በፌደራል ደረጃ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ፣ እንዲሁም በክልል ቢሮዎች በመተግበር ላይ ሲሆን ለምሳሌ፡-በቤ.ጉ.ክ.መ በአማርኛ፣  በኦሮምኛ፣ በሽናሽኛ፣ በርትኛ እና በጉሙዝኛ ቋንቋዎች፣ አገልግሎት በመስጠት ለያ ይገኛል፡፡

 

 በመላዉ አለም የኢንተርኔት አገልግሎት ባለበት ቦታ ሁሉ ትኩስ አገራዊ የገበያ መረጃን በድህረ-ገፅ ማግኘት ያስችላል፡፡

Share