Promotion News

የባሕር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት አካዳሚክ ካውንስል በ27/12/2007 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ዶ/ር ተሾመ ሙላቴ ቦጋለ ከሌክቸረርንት ወደ ረዳት-ኘሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲያድጉ ወስኗል፡፡

ዶ/ር ተሾመ ሙላቴ ቦጋለ ፡ በሜካኒካልና ኢንደስትሪያል ምህንድስና ፋኩልቲ መምህር ሲሆኑ የ“PhD” ትምህርታቸውን በ“Mechanical Engineering” ታይዋን ሀገር ከሚገኘው National Taiwan Science and Technology University አጠናቀው ስለተመለሱ ይህ የደረጃ ዕድገት ተሰጥቷቸዋል ፡፡ በመሆኑም ኢንስቲትዩቱ ይህንን የማዕረግ እድገት ሲያበስር ቀጣዩ ጊዜ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንልዎ እየተመኘ፡ በቀጣዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመንግስት የተጣለባቸውን የመማር ማስተማር፤የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ሐላፊነት በመገንዘብ ያለዎትን ዕውቀትና ልምድ በመጠቀም የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በማሳሰብ ጭምር ነው፡፡

12/02/2008 ዓ.ም   

Date: 
23 Oct 2015
Image: 
Place: 
ባሕር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት
Share