በባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የአፕላይድ ሂውማን ኒውትሪሽን (Applied Human Nutrition) ትምህርት ክፍል ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራን በኒውትሪሽን መረጃ ትንተና ሶፍትዌር ላይ ስልጠና ሰጠ

በኢንስቲትዩቱ የአፕላይድ ሂውማን ኒዉትሬሽን ትምህርት ክፍል አዘጋጅነት ለ28 የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራን በኒውትሪሽን  መረጃ ትንተና ሶፍት-ዌር ላይ ከመጋቢት 13 እስከ መጋቢት 15/2011 ዓ.ም የተሰጠው ይህ ስልጠና የመምህራንን የምርምር አቅም ከመገንባት አንፃር መረጃ ለመተንተን የሚያስችሉ ሶፍትዌሮችን መጠቀም እንዲችሉ ለማድረግ ታስቦ የተሰጠ መሆኑን የትምህርት ክፍሉ ተጠሪ ዶ/ር መስፍን ወጋየሁ ገልፅዋል፡፡ 
ስልጠናውን የሰጡት በትምህርት ክፍሉ የድህረ መረቃ ፕሮግራም ላይ ኮርሶችንና ሴሚናሮችን በመስጠት የሚተባበሩት በጅማ  ዩኒቨርስቲ መምህርና ተመራማሪ እንዲሁም በፌደራል ደረጃ የምግብ እና ኒውትሬሽን  ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች አማካሪ የሆኑት ታዋቂዉ ሙሁር ፕሮፎሰር ተፈራ በላቸዉ ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት በሰጡበት ወቅት ባሰሙት ንግግር መምህራን ስልጠናውን በተገቢው መንገድ የጨበጡ መሆናቸውን ገልፀው ለተግባራዊነቱ ደግሞ ቁርጠኝነት በመውሰድ ስራ ላይ ለማዋል ተነሳሽነት እንዲኖራቸው እያሳሰቡ ሌሎች ተመሳሳይ ስልጠናዎች እና የአቅም ግንባታ ስራዎች ሲኖሩ እገዛቸውን ለማበርከት ፈቃደኛ መሆናቸውን  ገልጸዋል፡፡ 

Share