ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮችንና አስተዳዳሪዎችን ለመሰየም በወጣ መመሪያ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶችን የአመራር እና አሰራር ነፃነት ለመደንገግ በወጣ መመሪያ (IOT’s Autonomy Directive)መሰረት ለባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማኔጂንግ ዳይሬክተር  የሃለፊነት ቦታ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመሾም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡

1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡- የሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ  በኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ወይም በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በፋይናንስ፣ በአካውንቲንግ፣ በኢኮኖሚክስ፣  በማኔጅመንት ወይም ተመሳሳይ የትምህርት መስክ ያለው/ያላት

2ኛ. የስራ ልምድ ፡- ከመጀመሪያ ዲግሪ በኋላ በሙያው ቢያንስ 6 ዓመት ያገለገለ/ ያገለገለች    

3ኛ. የአመራርነት የስራ ልምድ፡- ቢያንስ 3 ዓመት በአመራርነት ያገለገለ/ ያገለገለች

4ኛ. የተቋሙን ዓላማ ለማሳካት የሚያግዙ አስተዳደራዊ ዘርፎችን ውጤታማ ለማድረግና ዋና ተግባራቱን ለማስፈፀም የሚያቀረቡት አጭር የስራ እቅድ /ንድፈ ሃሳብ/ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል

5ኛ. የተቋሙ ማህበረሰብ ተወካዮች እንዲሁም የሴኔት አባላት እና ተጨማሪ አመራሮች በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ቀርቦ/ባ ገለፃ ማድረግ እና ማብራሪያ  መስጠት የሚችል/የምትችል

6ኛ. ዜግነት፡ ኢትዮጵያዊ/ት

7ኛ. ደመወዝና ጥቅማጥቅም፡- ደመወዝ በተቋሙ ስኬል መሰረት ሆኖ ለቦታው የተፈቀዱ ሌሎች ጥቅማጥቅሞች የሚከፈሉ ይሆናል፡፡ 

8ኛ. ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡

አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ፡ ቀጥሎ ከተራ ቁጥር I - V የተዘረዘሩትን መረጃዎች፡

  1. ማመልከቻ
  2. ሲቪ (CV)  
  3. የትምህርት ዝግጅት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ
  4. የስራና የአመራርነት ልምድ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ
  5. ዋና ተግባራቱን ለማስፈፀም የሚያቀርቡት አጭር የስራ እቅድ /ንድፈ ሃሳብ/

በባሕርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኢንፎረሜሽንና ስተራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በተወካይ አማካኝነት በተዘጋጃው የማመልከቻ መረካከቢያ ቅፅ ላይ  በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች: +251- 911 37 94 22/ +251-588 209338 ደውሎ ወይም በአካል ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡ የስራ መደቡን ተግባር እና ሃላፊነት በተቋሙ ድረ ገጽ http://bit.bdu.edu.et/managing-director ማግኘት ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ

  • አመልካቾች ዋና ተግባራቱን ለማስፈፀም የሚያቀርቡት አጭር የስራ እቅድ ፅሁፍ/ንድፈ ሃሳብ/ ከ 5 ገፅ ያልበለጠ፡ ሆኖ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚዘጋጅ ሲሆን፡ Power Geez Unicode1/Times New Roman የፅሁፍ መጠን 12 የሆነ፡ በመስመር መካከል ያለ ስፋት 1.5 የሆነና ማሪጂን/የጠርዝ ክፍተት (ከቀኝም፡ ከግራም፡ ከላይም፡ ከታችም ፡ 1 ) መሆን አለበት፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሱፐርቫይዘሪ ቦርድ

Date: 
Thu, 07/04/2019
Place: 
Bahir Dar Institute of Technology Bahir Dar University
Share