ዶ/ር ቢምረዉ ታምራት የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ25/11/2011 በጃካራንዳ ሆቴል በተደረገ ፐሮግራም ዶ/ር ቢምረዉ አዲሱ ማኔጂንግ ዳይሬክቶር አደርጎ ሾሟል፡፡ በእለቱ በነባሩ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ማህሪ ቁምላችው እና አዲስ በተሾመት ዶ/ር ቢምረዉ መካከል የስልጣን ርክክብ የተደረገ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ  አድማሱ አቶ ማህሪን ለነበራቸዉ ቆይታ እና ላበረከቱት አስተዋፅኦ አመስግነዉ አዲስ ለተሾሙት ማኔጂንግ ዳይሬክተርም መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸዉ ተመኝተዋል፡፡

ተሰናባቹ ማኔጂንግ ዳይሬክቶር አቶ ማህሪ ቁምላችው ባደረጉት የስንብት ንግግር በሃላፊነት ዘመናችው የተቋሙ ማህበረሰብ ላደረገላቸዉ ቀና ትብብር አመስግነዉ በቀጣይም ባላቸዉ እዉቀት እና ልምድ ተቋሙን ለማገልገል ቃል ገብተዋል፡፡ ዶ/ር ቢምረዉም የአንድ ተቋም ጥንካሬ እና ዉጤታማነት በአንድ ግልሰብ  ብቻ ስለማይወሰን ለተቋማችን ስኬት የአብረን እንስራ መልእክት ለሁሉም የተቋሙ ማህበረሰብ አስተላልፈዋል፡፡

images: 
Share