ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

Body: 

ቀን፡ 11/06/2016 ዓ.ም

 

ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጅ እና የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ተቋማትን አመራሮች እና አስተዳዳሪዎች ለመምረጥና ለመሰየም ነሃሴ/2013ዓ.ም የወጣውን መመሪያ ቁጥር 01/2021 መሰረት በማድረግ ለባሕር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት:-

(1ኛ) የአካዳሚክ ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር እና

(2ኛ) የምርምርና የማህበሰብ አገልግሎት ምክትል ሳይንፊክ ዳይሬክተር

የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ማገልገል የሚችሉ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡

የመወዳደሪያ መስፈርት፡-

1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡- በምህንድስና፣ በቴክኖሎጅ ፤ እና በሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ሌክቸረር እና ከዚያ በላይ የሆነ/የሆነች፤

2ኛ. የስራ ልምድ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ በኋላ 6 ዓመትና ከዚያ በላይ ልምድ ያለው/ያላት፣

3ኛ. የስራ እና የአመራርነት ልምድ፡-

                     · ሶስተኛ ዲግሪ ያለዉ/ያላት እና በዲፓርትመንት ሃላፊ ደረጃ እና ከዚያ በላይ በሆነ አመራርነት 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ ያገለገለ/ያገለገለች ወይም

                     · ሁለተኛ ዲግሪ ያለዉ/ያላት እና በዲፓርትመንት ሃላፊ እና ከዚያ በላይ በሆነ አመራርነት 5 አመት እና ከዚያ በላይ ያገለገለ/ያገለገለች፤

                        4ኛ. የተቋሙን ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እና ግብ ለማሳካት የሚያስችል ስልታዊ እቅድ (Strategic Plan) ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፤

                       5ኛ. የተቋሙን ማህበርሰብ ተወካዮች፣ የሴነት አባላት እና ተጨማሪ አመራሮች እንዲሁም ለአስመራጭ ኮሚቴ በሚገኙበት መድረኮች በስልታዊ ዕቅዱ ላይ በአካል ቀርቦ/ቀርባ ገለፃ ማድረግ እና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፤

                               6ኛ. ከማንኛዉም አይነት የዩኒቨርስቲ/የተቋም ፈቃድ (ዕረፍት፣ ትምህርት፣ ምርምር ወዘተውጭ የሆነ/የሆነች፤

አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ማለትም ከ12/06/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከታች ከተራ ቁጥር 1-5  የተዘረዘሩትን ማስራጃዎች/ሰነዶች በመያዝ እና ያመለከቱትን የሃላፊነት ቦታ በመጥቀስ ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኢንፎርሜሽንና ስታራቴጂክ ኮሚዩኒኬሼን ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተወካይ አማካኝነት በሚዘጋጀው የማመልከቻ መረካከቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት ማመልከት ይኖርባቸዋል፡፡

መሟላት ያለባቸው ሰነዶች፡-

1. ማመልከቻ ደብዳቤ፣

2. የግለ ታሪክ መግለጫ (CV)፣

3. የትምህርት ማስረጃ ኮፒ፣

4. ከሰዉ ሃይል አስተዳድር የተረጋገጠ የስራና የአመራርነት ልምድ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ፣

5. አጭር ስልታዊ እቅድ (Strategic Plan)፣

 

ለበለጠ መረጃ በሚከተለው ስልክ ቁጥር በ0993928910/0911901055 ደውለው ማነጋገር ወይም የተቋሙን ድረ-ገጽ bdu.edu.et እና bit.bdu.edu.et መመልከት ይችላሉ፡፡

ማሳሳቢያ

· አመልካቾች የሚያቀርቡት አጭር ስልታዊ ዕቅድ (Strategic Plan) ከ 05 ገፅ ያልበለጠ ሆኖ በአማርኛ ወይም በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚዘጋጅ ሲሆን Power Geez Unicode 1/Times New Roman ፎንት በመጠቀም የፅሁፉ መጠን 12  የሆነ፣ በፅሁፉ መስመር መካካል ያለው ስፋት 1.5 የሆነና ከአራቱም ጠርዝ (Margine)  ያለው ክፍተት 1 ኢንች መሆን አለበት።

· ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።

· አካል ጉዳተኛ አመልካቾች ከሚመለከተዉ አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸዉ።

 

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የሁለት ም/ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች አስመራጭ ኮሚቴ

 

 

                          

Date: 
Tuesday, February 20, 2024 - 12