የባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ለአዲስ ቅጥር መምህራን የሙያ ትውውቅ ስልጠና ሰጠ፡፡

የባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በ2008 ዓ.ም በከፍተኛ ውጤት ከተመረቁ ተማሪዎች መካከል 53 ተማሪዎችን ለመምህርነት ቀጠረ፡፡ለአዲስ ቅጥር መምህራንም የአካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አበራ አስቻለው የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዴት መከናወን እንዳለበት እና ስለ ባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ስትራቴጅክ እቅድ ገለፃ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም የሰው ሃይል አስተዳደር ተወካይ አቶ ዘገየ መልካሙ የአዲስ ቅጥር መምህራን መብትና ግዴታ አብራርተው የመልካም ስነምግባር ባለቤት እንዲሆኑም አደራ ብለዋል፡፡

Share