የባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ለክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች የፕሮግራም ትውውቅ ስልጠና ሰጠ፡፡

የባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የተማሪዎች ዲን አቶ ጋሻው ፣ የሬጅስትራር ዳይሬክተር አቶ ተፈራ እንየው፣ የተከታታይና ርቀት ትምህርት አሰተባባሪ አቶ ጐሳ ዘውዴ፣ የኮምፒውቲንግ ፋካሊቲ ተጠሪ አቶ በለጠ ቢያዝን፣ የክረምት መርሀ ግብር ለሚማሩ ከ1000 በላይ ተማሪዎች ስለ ተቋሙ የሬጅስትራር አሰራር፣ ስለ ውጤት አያያዝ፣ ስለ ምዘና ስርአት እንዲሁም የፋኩሊቲው ተማሪ በመሆኑ የሚጠበቅበትን መብትና ግዴታ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ከተማሪዎቹ ለተነሱ ከምግብ፣ ከአልጋ እና ተያያዥ ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

Share