የሳይንስና ቴክኖሎጅ ሚንስተር ሚንስትር ከባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዪት መምህራንና ቴክኒካል አሲስታት ጋር ውይይት አደረጉ

የሳይንስና ቴክኖሎጅ ሚንስተር ሚንስትር  የተከበሩ ዶ/ር ኢንጅነር  ጌታሁን መኩሪያ በሀገሪቱ የሳይንስና ቴክኖሎጅ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ ዙርያ  ከባህር ዳር  ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዪት መምህራንና ቴክኒካል አሲስታት ጋር ውይይት አደረጉ ፡፡

ሚንስትሩ በአገራችን የቴክኖሎጂ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት ብሔራዊ የቴክኖሎጂ ፍኖተ ካርታ ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡ ለቴክኖሎጅ ሽግግር የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ግብአቶች የተጠቀሱ ሲሆኑ የግብርና ግብአቶች ላይ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ምርታማነትን ማሳደግ ፣ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ መሸጋገር እንዲሁም ለዚህ ተምሳሌት የሆኑ አገሮች ለአብነት ቀርበዋል፡፡

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች ሚኒስትሩ ምላሽ የሰጡ ሲሆን በቀጣይም ከዩኒቨርስቲው ጋር በትብብር በመስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

 

 

images: 
Share