በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች ፣ መምህራንና ሰራኞች ታላቁን የኢትዮጵ ህዳሴ ግድብ ጎበኙ

የተቋሙ 162 መምህራንና ሰራተኞች እና 54 የሲቪልና ውሃ ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ከግንቦት 18- 20/2009 ዓ/ም የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱም ፣ ተማሪዎች ፣መምህራንና ሰራተኞች ግድቡ ያለበትን ደረጃ ከመጎብኘት ባሻገር ሙያዊ ማብራሪያ የሚሹ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት ከአስጎብኝዎች ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ እንደገለፁት በትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጡትን ምህንድስና ነክት ምህርቶችንና ንድፍ ሀሳብ ስራችን እዚህ በአካል (በተግባር) ለማየት በመምጣታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ሰፋ ያለ ሙያዊ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ንጉስ ጋብዩ ለኢንጅነር ስመኘው በቀለ ስጦታ አበርክተዋል፡፡

Share