ለትምህርት ፈላጊዎች

ከአሁን በፊት ዩኒቨርሲቲው ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ከ03/11/2009 ዓ.ም እስከ 12/12/2009 ዓ.ም ድረስ ለሶስተኛ እና ሁለተኛ ዲግሪ ምዝገባ ያካሄድን እና በ19/12/2009 ዓ.ም ፈተና ያሰጠን መሆናችን ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ በተለያዬ ምክንያት ሳይመዘገቡ የቀሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን እድል ለመስጠት ሲባል ተጨማሪ ማስታወቂያ በማውጣት አመልካቾችን መመዝገብ ታምኖበታል፡፡ ስለሆነም ከአሁን በፊት ለሶስተኛ እና ሁለተኛ ዲግር በወጡት ዲፓርትመንቶች መመዝገብ ለምትፈልጉ አመልካቾች የምዝገባ ቀን ከነሀሴ 30 እስከ ጳጉሜ 01/2009 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በዕለቱ በመመዝገብ ጳጉሜ 03/2009 ዓ.ም ፈተና እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ለምዝገባ ስትመጡ የትምህርት ማስረጃችሁን ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ
  • የመመዝገቢያ 50 ብር
  • ኢፊሻል ትራንስክሪፕት ከምዝገባ በፊት ሬጅስትራር ቀድሞ መድረስ አለበት

ኢፊሻል ያዘዙበትን ደረሰኝ፣ የወጪ መጋራት የከፈሉበትን ደብዳቤ እና ደረሰኝ ይዞ ምዝገባ ይካሄድልኝ ማለት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Date: 
Tue, 09/05/2017
Place: 
Bahir Dar Institute Of Technology
Share