የግብርና ኬሚካሎች አጠቃቀም በዉሃ እና በሰብል አካላት ላይ የሚያደርሰዉ ተፅዕኖ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ተካሄደ

የባህርዳር ቴክኖሎጂ ተቋም ነሃሴ 23/2011 ዓ/ም የግብርና ኬሚካሎች አጠቃቀም በዉሃ እና በሰብል አካላት ላይ የሚያደርሰዉ ተፅዕኖ አስመልክቶ ከዳንግላ እና መቂት ወረዳ ከመጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ፡፡ በዉይይቱ የተቋሙ ኬሚካልና ምግብ ምህድስና መምህርና ተመራማሪ አቶ ፈለቀ ሽቱ የግብርና ኬሚካሎች አጠቃቀም በዉሃ እና በሰብል አካላት ላይ የሚያደርሰዉ ተፅዕኖ በተመለከተ በአካባቢዉ ላይ ያደረጉትን የምርምር ዉጤት ያቀረቡ ሲሆን በምርምር ፅኁፋቸዉም በሰዉ ፣እንስሳት፣ በሰብል፣ እንዲሁም በተፈጥሮ ላይ ኬሚካሎቹ የሚያመደርሱትን ተጽእኖ በሰፊዉ ዳሰዋል፡፡

በዉይይቱ ተሳታፊ የነበሩ ባለድርሻ አካላት የችግሩን አሳሳቢነት ተረድተዉ አማራጭ የሰብል ማዳበሪያ ዘዴዎች እንደሚያስፈልጋቸዉ እና ህገወጥ ኬሚካል ነጋዴዎች ላይ ጠንከር ያለ የህግ ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡ ከመድረክም በክልል ደረጃ ከፍተኛ የህግ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን እና ህብረተሰቡም እራሱን ከህገዎጦች በመከላከል አስፈላጊዉን ጥቆማ እንዲሰጥ እና ተፈጥሮአዊ የሆኑ ዘዴዎችን እንደ አማራጭ ሰብል ማዳበሪያነት እንዲጠቀሙ ምክረ ሀሳብ ተሰጥቷል፡፡

images: 
Share