የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዓመታዊ የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽንና አካሄደ

የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በየአመቱ የሚያካሂደውን የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ከሰኔ 27-28፡ 2011 ዓ ም በፖሊ ግቢ በደማቅ ሁኔታ ትካሂዷል፡፡ በፕሮግራሙ በተቋሙ ተማሪዎችና መምህራን በጠቅላላ 57 የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ቀርበው ለእይታ በቅተዋል፡፡

በቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽኑ ላይ በባህር ዳርና አካባቢዋ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች፡ የሙያና ቴክኒክ ማሰልጠኛ ተቋማት፡ የክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶችና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል፡፡

ከቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን በተጓዳኝም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን በውይይቱም ቴክኖሎጂወችን ወደስራ ለማሽጋገር ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ እንድሚገባ አጽንሆት በመስጠት ተጠናቋል፡፡

images: 
Share