የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የማህበረስብ አገልግሎት ጽ/ቤት የወጪ ቆጣቢ የመማሪያ ክፍሎችን አስገንብቶ አስረከበ

በባህር ዳር ዩንቨርስቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የማህበረስብ አገልግሎት ጽ/ቤት በፎገራ ወረዳ ወርቅ ሜዳ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ከአካባቢው በሚገኙ ቁሳቁሶች የወጪ ቆጣቢ ግንባታ ማስተዋወቂያ ት/ቤት አስገንብቶ  አስረክቧል።  ጽ/ቤቱ ከአካባቢው በሚገኙ ቁሳቁሶች (ቀርቀሀ ፣ አግሮስቶን እና የግንባታ ቁሶች)ሶስት የመማሪያ ክፍሎችን በአነስተኛ ወጪ አስርቶ በተቋሙ ዳይሬክተር ዶ/ር ንጉስ ጋብዬ በተገኙበት ርክክቡ ተፈጽሟል።

Images: 
Share