ለነባርና አዲስ ገቢ የባህርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች በሙሉ

ትምህርት ሚኒስትር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ባወጣው የመግቢያ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የነባርና የአዲስ ገቢ ተማሪዎችን መግቢያ ቀን ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን የባህርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (Bahir Dar Institute of Technology-BiT) ከ1ኛ እሰከ 3ኛ አመት ያሉ ተማሪዎች በ2010 ዓ.ም 2ኛ ሴሚስተር ላይ የሚሰጠውን የማጠቃለያ ፈተና ሳይፈተኑ በመሄዳቸው ምክንያት በአሁኑ ወቅት በ2010 ዓ.ም 1ኛ እና 2ኛ አመት ለነበሩ ተማሪዎች ፈተናው ተማሪዎቹ በነበሩበት ግቢ/campus/ እየተሰጠ በመሆኑ እና የመኝታ እጥረት ስላጋጠመ የ 2011 ዓ.ም አዲስ ገቢ እና በ 2010 ዓ.ም 2ኛ ሴሚስቴር ላይ ማጠቃለያ ፈተና ያልወሰዱ የ3ኛ ዓመት ተማሪዎችን የመግቢያ ጊዜ ማስተካከል አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ብቻ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

Date: 
20 Oct 2018
File Attachment: 
Place: 
ባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
Share