ስለ “Reverse Engineering” የግማሽ ቀን ትምርታዊ-ጉባኤ ተካሄደ

በኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ምህንድስና ፋኩልቲ አሰናጅነት “Reverse Engineering” ን የተመለከተ የግማሽ ቀን ትምህርታዊ ጉባኤ ተካሂዷል፡፡ በጉባኤው “በቪዲዮ ኮንፈረንስ” ገለፃ ያደረጉት ነዋሪነታቸው በአሜሪካ የሆነው ዶ/ር ካሰኝ ገ/ፃዲቅ ሲሆኑ በገለፃቸው የ “Reverse Engineering” ን ምንነትና እንዴትነት አስረድተዋል፡፡ በዚህም መሰረት “Reverse Engineering” አንድ የተሰራን ነገር የተሰራበትን አኳኋን ለመረዳት አፈራርሰን የምናይበት መንገድ መሆኑን ጠቁመው በአመዛኙ የተሰራውን ነገር ለማላመድና ለማሻሻል የምንጠቀምበት መሆኑን በገለፃቸው አንስተዋል፡፡ የተሰራውን ነገር ከማፈራረስ መልሶ እስከመገጣጠም ድረስ ያለውን መሰረታዊ ዕውቀቶችንም ደረጃ በደረጃ አስረድተዋል፡፡ በትምህርታዊ-ጉባኤው የአራተኛና አምስተኛ ዓመት የኤልክትሪካልና ኮምፒውተር ምህንድስና ተማሪዎችና መምህራን የተሳተፉበት ሲሆን ጥያቄዎች ተነስተው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የትምህርታዊ ጉባኤው አላማም ተማሪዎች የመንፈቅ-ዓመትና የመመረቂያ ፕሮጀክቶቻውን ሲሰሩ በብዙ አገራት የተለመደውን የ“Reverse Engineering” ልምምድ እንዲሞከሩ ለማበረታት መሆኑን የፋኩልቲው መምህርና የሃይልና ኢነርጂ ት/ክፍል “ቼር” አቶ ዮሴፍ ብርሃን ለኢስኮ ተናግረዋል፡፡

images: 
Share