በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የICT4D የምርምር ማዕከል “Advanced Web Design and Development/ full-stack” በሚል ርዕስ ስልጠና ሰጠ

የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የICT4D የምርምር ማዕከል ከTargeted Institute of Technology ጋር በመሆን “Advanced Web Design and Development/ full-stack” በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን ኦንላይን ሥልጠና አጠናቀቀ። ስልጠናውም Basics of HTML፣ CSS፣ Web development with WordPress፣ Introduction of Databases with MySQL፣ Javascript፣ Node.js የሚሉ ርዕሶች የተካተቱበት እንደ ነበር እና በሥልጠናውም ሰልጣኞቹ የተማሩትን የሚተገብሩባቸው የተለያዩ ተግባራዊ ልምምዶችና ፕሮጀክቶች እንደተሰጡ ተገልጿል። ተጨማሪ ያንብቡ