BiT Snapshot

Featured News

የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ቢሮ በያዝነው አመት የተከናወኑ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ይፋ አደረገ፡፡ ቢሮው በያዝነው አመት ተከናወኑ ያላቸው ስራወችን እንደሚከተለው አቅርቧል፡- • ለአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ እና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ በተለያዩ ምክንያቶችና በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት የብረት ድስት ማምረቻ ማሽን “Deep Drawing Machine” ችግር ገጥሞት ማምረት ያልቻለ በመሆኑ ሙያዊ ድጋፍ በጠየቁት መሰረት ከፍተኛ ወጭ የሚያስወጣ ማሽን በማህበረሰብ አገልግሎት በነፃ በሜካኒካልና ኢንዱስትሪያል ፋኩልቲ መምህራን ተስተካክሎ ስራ ጀምሯል፡፡ • ለጣና ሐይቅ እና ፋሲሎ 2ተኛ ደረጃና መሰናዶ ትም/ቤት የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ሴት ተማሪዎች “How to Take Online National Examination” በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች የዋጋ ትመናና አወጋገድ ፕሮጀክት ስራ አጠናቆ ይፋዊ የርክክብ ስርዓት አካሄደ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ጋር የካቲት 12/2012ዓ.ም በወሰደዉ የስራ ዉል መሰረት የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች የዋጋ ትመናና አወጋገድ ፕሮጀክት ስራ አጠናቆ ስለማስረከቡ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ይፋዊ የርክክብ ስርዓቱንም በጥር 08/ 2013 ዓ.ም. አካሂዷል፡፡ የርክክብ ስነ-ስርዓቱ በባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ እና በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ማተቤ አዲስ አማካኝነት የተፈፀመ ሲሆን ሌሎችም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፋኩልቲ ዲኖችና መምህራን ስነ-ስርዓቱን ተካፍለዋል፡፡
የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከሃሙሲት እስቴ የአስፓልት መንገድ ስራ መጀመርን አስመልክቶ በተዘጋጀ የምስጋና ፕሮግራም ላይ ተሳተፈ፡፡ ከሃሙሲት እስቴ ከተማ የሚሰራውን የአስፓልት መንገድ ስራ መጀመር አስመልክቶ በደራ ወረዳ አርብ ገበያ ከተማ በጥር 09/ 2013 ዓ.ም. በተዘጋጀው ፕሮግራም የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ባንተላይ ስንታየሁ እና የመንገድ ዲዛይን ማማከር ስራውን በባለሙያነት እና አስተባባሪነት የመሩት ኢንጂኒየር ይመር ደጉ የተገኙ ሲሆን በመድረኩም ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በዲዛይን የማማከር ስራ ላደረገው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ምስጋና ቀርቦለታል፡፡ በተለይም ለኢንጂኒየር ይመር ደጉ የምስጋና ስጦታ ከአዘጋጅ ኮሚቴወች ተበርክቶላቸዋል፡፡ በምስጋና ፕሮግራሙ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር ፋንታ ማንደፍሮ እና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር ኢንጂኒየር ሀብታሙ ተገኝን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ባለስልጣናት መገኘታቸው ታውቋል፡፡
የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በክቡር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር አህመዲን መሀመድ ከተመራው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ቡድን ጋር የምክክር መርሀ-ግብር አካሄደ፡፡ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር የዲጂታል 2025 ቡድን ጋር በ 24/04/13 ዓ.ም. የተካሄደውን የምክክር መርሀ-ግብር የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ አስተዋውቀው የከፈቱ ሲሆን የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አክለውም በአገርአቀፍ ደረጃ ትልቅ ቦታ በተሰጠው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚንስቴር ዐብይ ተግባራትን እያከናወኑ እንደመሆናቸው በሁለቱ መካከል ከሚደረጉ የምክክር መርሀ-ግብሮች ወሳኝነት ባሻገር በተግባር የተደገፈ ቅንጅታዊ አሰራር ሊኖር እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩንቨርስቲ ለዱርቤቴ ከተማ ማህበረሰብ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ሰርቶ አስረከበ የኢንስቲትዩቱ የሲቪልና ውሃ ምህንድስና ፋኩልቲ ፈቃደኛ ባለሙያዎችን ከየዘርፉ በማሠባሠብ የፕሮጀክት ጥናትና ዲዛይን ቡድን በማዋቀር እና ከወረዳ አስተዳደሩና የህብረተሰብ ተወካዩች ጋር በመመካከር ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ በሠጠው መሠረት ቡድኑ የፕሮጀክቱን ጥናትና ዲዛይን ስራ የውል ሠነድ ዝግጅትን ጨምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለከተማ አስተዳደር አስረክቧል፡፡ በመቀጠልም የተሰራዉን ንድፈ ሃሳብ ወደመሬት እንዲወርድ የፍይናንስ ምንጩ ከህብረተሰቡ ተሳትፎ በመሆኑና ካለ ፍላጎት የተነሳ የፕሮጀክት ጥናትና ዲዛይን ቡድኑ ለጨረታ ኮሚቴው በጨረታው ሂደት የሚያስፈልገውን ሠነዶች የማዘጋጀትና ሙያዊ የማማከር እገዛ የማድረግ ሥራ ሠርቷል፡፡ በዚህም መሰረት አሽናፊው ተቋራጭ (IFH ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር) ውል ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ሥራ እንዲገባና በውሉ መሠረት የፕሮጀክት ሥራውን የከተማ አስተዳደሩ ባለሙያዎችን በመጨመር ውሉ በሚጠይቀው መሠረት የፕሮጀክቱን የማማከር ሥራ በትኩረትና በጥልቅ ሙያዊ ዲስፕሊን በመከታተል ችግሮችን በጊዜ
የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ጀመረ በኢንስቲትዩቱ ዉስጥ በሚገኙ ሁሉም የትምህርት ክፍሎች የ2012 ዓ.ም መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች መማር ማስተማር ከ05/04/2013 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት ተጀምሯል፡፡ ሁሉም የተመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸዉ ላይ በመገኘት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ መማር ማስተማሩ በታቀደዉ መሰረት እንዲቀጥልም ሁሉም ፋኩልቲዎች የክትትል እና ቁጥጥር ስራዉን ባላሰለሰ መልኩ ከወዲሁ ጀምረዋል፡፡
የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች የዋጋ ትመናና አወጋገድ ፕሮጀክት ስራ አጠናቆ አስረከበ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ጋር የካቲት 12/2012ዓ.ም በወሰደዉ የስራ ዉል መሰረት የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች የዋጋ ትመናና አወጋገድ ፕሮጀክት ስራ አጠናቆ አስረከበ፡፡ በፕሮጀክቱ እቅድ መሰረት በተከናወነው የዳሰሳ ጥናት፣ በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ እና በበለፀገው የመተግበሪያ ሶፍትዌር ዙሪያ በባህር ዳር እና አዲስ አበባ ተከታታይ ዉይይቶች እና ግምገማ ሲካሄድ ከቆየ በኋላ በአዳማ ከተማ በተካሄደው አገር አቀፍ የውይይት መድረክ ላይ በማቅረብ የተገኘውን ግብአት በማካተት አጠቃሎ አስረክቧል፡፡
የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኮረና ቫይረስ ወደአገራችን መግባቱን ተከትሎ በፌደራል መንግስት ዉሳኔ ተማሪዎች ወደ መጡበት አካባቢ ከተሸኙበት ቀን ጀምሮ ተማሪዎችን እንደገና ተቀብሎ መማር ማስተማሩን ለማስቀጠል የሚያስችሉ መጠነሰፊ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በተለይ ደግሞ የካረና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እና ለመከላከል የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር እና ከንክኪ ነፃ የሆኑ የእጅ መታጠቢያ ጨምሮ መጠነ ሰፊ ቴክኖሎጂዎችን ለኢንስቲትዩቱ እና አካባቢዉ ማህበረሰብ ሰርቶ አበርክቷል፡፡ በ2013 ዓ.ም የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር ኮረናን እየተከላከሉ ትምህርትን ለማስቀመጥ ባወጣዉ አቅጣጫ መሰረት ኢንስቲትዩቱ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን ከታህሳስ 01 እስከ 02 2013 ዓ.ም መቀበል ጀምሯል፡፡
የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በጋራ ሊሰራባቸዉ ስለሚችሉ የምርምር እና ፕሮጀክት ሃሳቦች ላይ ተወያይቷል የኢንስቲትዩቱ ከበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና የየባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮች በ26/03/2013 ዓ.ም በስኳር ልማት ዘርፍ እና ተዛማጅ የምርምር አቅጣጫዎች ላይ ሰፋ ያለ ዉይይት አካሂዷል፡፡ በዉይይቱም የበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክ ዳይሬክተር ስራ-አስኬያጅ አቶ አንተነህ አሰጌ፣ የፕሮጀክቱ ምርምር ዘርፍ ሃላፊ ዝናዉ ድልነሳ እንዲሁም ሌሎች የማኔጅመንት አባላት የተገኙ ሲሆን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዉን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬዉ ተገኝ እና ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዉበታል፡፡ ለዉይይቱ መነሻ የሚሆን ፅሁፍ በበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ምርምር ዘርፍ ቀርቧል፡፡ በፅሁፉም ከበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት አንፃር የትምህርት እና ምርምር ተቋማት ተሳታፊ ሊሆኑባቸዉ የሚችሉት የምርምር አቅጣጫዎች ተመላክተዋል፡፡

Pages