BiT Snapshot

Bahir Dar Institute of Technology newsletter

Bahir Dar Institute of Technology newsletter categories.

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አመራሮች የበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ፣ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ተስፋየ ሽፈራው እና የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዝደንት ወ/ሮ ገዳም ማንደፍሮን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በየካቲት 09/2013 ዓ.ም. የበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል፡፡ ጉብኝቱን አቶ አንተነህ አሰጌ የበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ እና አቶ ተባበል ካሳው በፕሮጀክቱ የፋብሪካ ኦፐሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ የመሩ ሲሆን አሁን ላይ የደረሰበትን ቁመና ለጎብኝዎቹ አስመልክተዋል፡፡
Share

Bahir Dar University has signed Memorandum of Understanding with Beles Sugar Development Project Office

The Memorandum of Understanding (MoU) has been signed by Mr. Anteneh Asegie, General Manager of Beles Sugar Development Project and Dr. Tesfaye Shiferaw, Vice President for Research and Community Service of Bahir Dar University representing Dr. Firew Tegegne, President of Bahir Dar University on February 16, 2021. The MoU reflects the parties’ sincere and genuine intensions to collaborate in specific activities set out there pertaining to the areas of research, design and development, technology transfer,
Share

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የቢዝነስ ኢንኩቤሽን እና የቴክኖሎጂ ስራ ፈጠራ ማዕከል ለተመራቂዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ

“Learn to build your own business idea and learn how to sell it” በሚል ርዕስ ከየካቲት 08/2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት የሚሰጠውን ስልጠና የኢንስቲትዩቱ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር መኳንንት አገኘሁ በአካል ተገኝተው ከፍተዋል፡፡ በመክፈቻው ፕሮግራም ላይ ዶ/ር መኳንንት እንደተናገሩት ማዕከሉ ከተቋቋመበት አጭር ጊዜ ጀምሮ ላከናወናቸው ተግባራት እውቅና ሰጥተው ሰልጣኞቹ ይህንን የስልጠና ዕድል በሚገባ ተጠቅመው የስራ ፈጠራ ሃሳባቸውን ከፍ ወዳለ ደረጃ የሚያሸጋግሩበት መድረክ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት የገለጹ ሲሆን ለgiz እና መሰል ድጋፍ አድራጊ ተቋማት በኢንስቲትዩቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ሄኖክ መብራቴ በበኩላቸው ስለ ማዕከሉ አጭር ገለፃ አቅርበው የስልጠናውን ዋና አላማ እና ዝርዝር መርሃ-ግብር ለሰልጣኞች በማስተዋወቅ ስልጠናውን አስቀጥለዋል፡፡
Share

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመተባበር ባዘጋጁት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ አመራር ስልጠና መድረክ ላይ የባህር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፕሮጀክት ኤግዚቢሽን አቀረበ

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ቤተ-መፅሀፍት የሆነው ጃን ሞስኮቭ ላይብራሪ የስልጠናውን የከሰዓት በኋላ መርሃ-ግብሮች ያስተናገደ ሲሆን በውስጡ በሚገኙት አምስት የተለያዩ አዳራሾች የቡድን ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡ በውይይት መድረኮቹ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚደንቶች እና ሌሎች አመራሮች እንዲሁም ከባለ ድርሻ አካላት የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተካተቱባቸው ሲሆን የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያሰናዳቸውን የዚህ አመት ተመራቂዎች የሰሯቸውን የተመረጡ የመመረቂያ ፕሮጀክቶች እና በተለያዩ ፋኩልቲዎች የተሰሩ የማህበረሰብ አገልግሎት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ፕሮጀክቶችን ያካተቱ ኤግዚቢሽኖች በረፍት ሰዓቶች ለተሳታፊዎቹ አቅርቧል፡፡
Share

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን የቢዝነስ ኢንኩቤሽንና የቴክኖሎጂ ስራ ፈጠራ ማዕከል (BiTec) ጎበኙ

ክቡር ሚኒስትሩ በየካቲት 04/2013 ዓ.ም. በማዕከሉ ተገኝተው የቴክኖሎጂ ስራ ውጤቶችን የጎበኙ ሲሆን የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ እና የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲፊክ ፕሬዝደንት ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ ጉብኝቱን መርተዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተሞክሮ አበረታች መሆኑን ጠቁመው ለሌሎች ዩኒቨርሲቲወችም እንደ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል አመላክተዋል፡፡
Share

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመተባበር ያዘጋጁት ለኮንስትራክሽን ባለሙያወች ሲሰጥ የነበረው ተግባር ተኮር ስልጠና ተጠናቀቀ

ስልጠናው ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለሙያዎች ከጥር 14/2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ 17 ቀናት በባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሲቪል እና ውሃ ሃብት ምህንድስና ፋኩልቲ ላቦራቶሪዎች የተሰጠ ሲሆን በፋኩልቲው መምህራን እና ቴክኒካል አሲስታንቶች አማካኝነት መከናወኑ ታውቋል፡፡ ስልጠናውን በስኬት ላጠናቀቁ ሰልጣኞች በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ዙሪያ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ሲምፖዚየም እና ኤግዚቢሽን መድረክ ላይ በተገኙት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር መስፍን አሰፋ እና በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ የእውቅና ሰርቲፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
Share

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያየየ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

በባህርዳር ነዩኒቨርሲቲ በነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም. 7520 ተማሪዎችን በበይነ መረብ ማስመረቁየሚታወስሲሆንበኮቪድ 19 ምክንያት የገፅ ለገፅ ትምህርቱ በመቋረጡ ምረቃቸው የተራዘመባቸውን ተማሪዎች ጨምሮ በአጠቃላይ 5117 ተማሪዎችን በጥር 29/2013 ዓ.ም. የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር በክብር እንግዳነት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡ ከነዚህም መካከል ባህርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያሰለጠናቸው 1320 መሆናቸው ታውቋል፡፡
Share

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳ በባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የማነቃቂያ ንግግር አቀረቡ

ዶ/ር ደረጀ እንግዳ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሙያ ማጎልበቻ ማዕከል በቀን 26/05/13 ዓ.ም. ባዘጋጀው መድረክ በሁለት የተለያዩ መርሃ-ግብሮች ንግግራቸውን ያቀረቡ ሲሆን በጥዋቱ ክፍለ ጊዜ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በተሳተፉበት መድረክ ‘‘የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች ሃላፊነትና ሚና በኢትዮጵያ እና መሰረታዊ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች ለምርምር ስራ’’ በሚል ርዕስ ሰፋ ያለ አነቃቂ ንግግር አቅርበዋል፡፡ በተለይም ስኮፐስ (Scopus) ከተባለው አለማቀፋዊ የ‘ሳይቴሽን ዳታ ቤዝ’ አገኘሁት ባሉት የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምርምር ውጤት ማሳያዎች (Research Impact Indicators) መረጃ ላይ ተመስርቶ በተለያዩ ሳይንሳዊ መመዘኛወች የተገመገመውን የኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ የምርምር ውጤት መገለጫ በስታቲስቲካዊ አቀራረብ አሳይተዋል፡፡
Share

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሙያ ማበልጸጊያ ማዕከል አዘጋጅነት ለተመራቂ ተማሪዎች የስራ ፍለጋ እና ተቀጣሪነት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

የሙያ ማበልጸያ ማዕከሉ ለ420 ተመራቂ ተማሪዎች ከጥር 22 እስከ ጥር 25/2013 ዓ.ም. ባሉት ተከታታይ ቀናት የስራ ፍለጋ እና ተቀጣሪነት ክህሎት ስልጠና አሰጥቷል፡፡ ስልጠናው በሁለት ዙር የተከናወነ ሲሆን ራስን መፈተሽ እና የተለያዩ የሙያ ዘርፎችን መዳሰስ፣ የስራ ፍለጋን ማቀድ፣ የትምህርትና ስራ ልምድ ማስረጃ (CV) ማዘጋጀት፣ የስራ ማመልከቻ አፃፃፍ፣ ለቃለ-መጠይቅ ራስን ማዘጋጀት፣ የቀረቡ የስራ እድሎችን መመዘን እና የመጀመሪያ የስራ ወቅትን መምራት የሚሉ ይዘቶች ተካትተውበታል፡፡ የክህሎት ስልጠናው በተግባር ተደግፎ ከአዲስ አበባ እና ጂማ ድረስ በመጡ የተመረጡ የPsychology እና Career Counseling ኤክስፐርቶች እና በሙያ ማበልጸጊያ ማዕከሉ አባላት አሰልጣኝነት ተከናውኗል፡፡
Share

የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከተመራቂ ተማሪዎች ገንቢ አስተያየት ተቀበለ

የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጥር 25/ 2013 ዓ.ም. ባዘጋጀው መድረክ ተመራቂ ተማሪወች በተቋሙ በነበራቸው ከ4 እስከ 5 ዓመት ቆይታቸው ያስተዋሏቸውን ጉድለቶችና መፍትሄወች ያሏቸውን ለኢንስቲትዩቱ አጋርተዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት አዲሱ የኢንስቲትዩቱ አካዳሚክ ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ደምሰው አልማው ለተመራቂወች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው አዲሱን የሃላፊነት ስራቸውን ከተመራቂ ተማሪዎች ጋር በመወያየት መጀመራቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡ ተመራቂዎቹ የሰጧቸው ገንቢ አስተያየቶችና ጥቆማዎችም ለወደፊት ስራቸው አጋዥ እና የትኩረት አቅጣጫዎችንም አመላካች ሆነው እንዳገኟቸው ጠቁመዋል፡፡
Share
Subscribe to RSS - Bahir Dar Institute of Technology newsletter