የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር እሰይ ከበደ በሱዳን ገዚራ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታዊ ሴሚናር አቀረቡ

================================
ትምህርታዊ ጉባኤውን የከፈቱት የገዚራ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ቫይስ ቻንስለር ሲሆኑ ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ልዑካን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በተለይም ም/ፕሬዝደንቱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ስልታዊ እቅድ መሰረት አድርገው ትምህርታዊ ገለጻ ማዘጋጀታቸው የሁለቱን ዩኒቨርሲቲዎች ወዳጅነት የሚያሳይና የሚያጠናክር መሆኑን ጠቁመው ከትምህርታዊ ገለጻውም  ገዚራ ዩኒቨርሲቲ ብዙ ቁምነገሮችን ሊቀስም እንደሚችል  ያላቸውን እምነት አጋርተዋል::
በመቀጠልም ዶ/ር እሰይ ከበደ መድረኩን በመረከብ የሱዳን ህዝብን እንግዳ ተቀባይነት አድንቀው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን አጠቃላይ መረጃ ካስጨበጡ በሗላ የዩኒቨርሲቲውን የአስር ዓመት ስልታዊ ዕቅድ መሰረት አድርገው ትምህርታዊ ገለጻውን አካሂደዋል:: በገለጻቸውም ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር በምርምርና ፈጠራ በቴክኖሎጂ ሽግግር በማህበረሰብ ተሳትፎ በመልካም አስተዳደርና መሰል ጉዳዮች ያስቀመጣቸውን ግቦች የአፈጻጸም ስልቶችና የውጤት ማሳያዎችን በማንሳት ሰፊ ገለጻ አካሂደዋል::
በመጨረሻም አለማቀፋዊነት ከዩኒቨርሲቲው ዋና እሴቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ረገድም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከገዚራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሁለቱን ወንድም ህዝቦች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ስራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል::
የገዚራ ዩኒቨርሲቲ ተሳታፊዎችም በቀረበው ርዕሰ ጉዳይ ዙርያ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን ያነሱ ሲሆን የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ታምራት ተስፋየ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ም/ሳ/ዳይሬክተር ዶ/ር መኳንንት አገኘሁ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር እሰይ ከበደ በቅደም ተከተል ምላሽ ሰጥተውባቸዋል::
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
 
  
Share