የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቅ አቶ ብርሓነ መዋ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ባዘጋጀው መርሀ ግብር ተገኝተው ሕዛባዊ ንግግር አቀረቡ።

 
[ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ኢስኮ/ባቴኢ]
*************************************
መርሃግብሩን የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ አቶ ብርሐነን በዚህ መንገድ በማግኘታችው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ከ 10 የሚበልጡ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪዎች መሆናቸው እነደሚያኮራቸው ተናግርው በተለይም የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የቀድሞ ምሩቃን እያደረጉት ላለው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ችረዋል::  አክለውም ኢትዮጵያ ታዳጊ ሀገር እደመሆና መጠን ኢንዱስትሪው ገና በመሆኑ እና አብዛኛው የተማርው ማህበረሰብ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደመገኘቱም በሚያከናውናቸው ምርምሮች ራስን ከማሳደግ ባለፈ ሕብረተሰቡን በመጥቀም በኩል አቅም እንዲኖረው በማድረግ ዩኒቨርሲቲዎች ብዙ ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል። 
አቶ ብርሓነ መዋ “Thinking outside the box but playing in the box” በሚል ባዘጋጁት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ያለውን ነባራዊ ችግር ተንትነው ወደፊት ሊስተካከሉ የሚችሉበት እድል ሰፊ እንደሆነ ገልጸዋል። የባሕል፣ የህዝብ ቁጥር እና የግል ፍላጎት ማየል በተለያየ መልኩ ሞራላችንን በመጉዳት ሰላም ማጣት ማስከትሉን ገልጸው ሙስና በከፍተኛ ደረጃ ሐገር እያመሳቀለ እንደሆነም ጠቁመዋል። በአንጻሩ መልካም ጅምሮች ያሉ መሆናቸው እና የተማረ ሰው የሚስፈልግበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን ጠቁመው ብዙ ርቀት መሄድ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል። በሌላ በኩል በስራ ፈጠራ ማዕከሉ የሚሰሩ ተማሪዎች ከሌሎች የሚለዩት ሲመረቁ ሐሳባቸውን እንጂ ራሳቸውን ስለማይሸጡ ነው ብለዋል። እንደ አቶ ብርሐነ ገለጻ በትምሕርት እና ልምድ የተገኘን እውቀት እና ክህሎት በጡረታ ይዞ መገለል እንደማይገባ በመግለጽ ለሌሎች ማካፈል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል:: ለመቀጠር የሚሄዱ ሰዎች በሂደት የሚገጥሟቸውን ነገሮች እና ችግሮች ለመፍታት ካሰቡባቸው የራስን ነገር ለመስራት እንደ እድል የሚቆጠር ይሆናል። ስለዚህም እየሰሩ ከማሰብ እያሰቡ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
አቶ ብርሐነ በውጪው ዓለም ለሚኖርው ማህበረሰብ ባስተላልፉት መልዕክታቸው ከትችት ይልቅ ሰርቶ መገኘት፣ ከማማረር ይልቅ ለውጥን መሻት የህሊና እረፍትን እንደሚያመጣ ገልጸው ሀገር በምትፈልጋቸው ጊዜ ሳይገኙ በጡረታ ወቅት ቤት ሰርተው ለመኖር የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ሊያስቡበት እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ተስፋ መቁረጥን በመተው በምንኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ችግር ለማጥፋት መታተር እና ለእኩልነት መሥራት የተሻለ እንደሆነ አብራርተዋል። 
በመጨረሻም በተሳታፊዎች በተነሱት ሓሳቦች ዙርያ ውይይት ተደረጎ መርሃግብሩ ተጠናቋል::
 
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
Share