ቢቴክ በማዕከሉ የተመረቱ የግብርና እቃዎችን ለተመረጡ የሴት አርሶ አደሮች አስረከበ

ቢቴክ በማዕከሉ የተመረቱ የግብርና እቃዎችን ለተመረጡ የሴት አርሶ አደሮች አስረከበ
[መጋቢት 28/2015 ዓ.ም፣ ባህር ዳር -ኢስኮ/ባቴኢ]
===============================
ቢዝነስና ኢንኩቤሽን የቴክኖሎጂ ስራ ፈጠራ ማዕከል ከ ሴንተር ፎር ግሎባል ኢኳሊቲ ጋር በመተባብር በተካሄደው አግሪቴክ ሃካቶን የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች ለማህበረስብ አገልግሎት እንዲውሉ በማሰብ ቀጣይ ፕሮጀችት ተነድፎ በዳንግሽጣ ቀበሌ ለተመረጡ ሴት እርሶአደሮች ማህበራት እንደ ቴክኖሎጅ ማላመድ የሚውሉ የበቆሎ መፈልፈያና የብረት ሲሎ አምርቶ አስረክቡል፡፡ በተጨማሪም ለማህበርሰቡ አባላት የስራ መፍጠር እና ቴክኖሎጅን ማሻገር ለማላመድ ሁለት በብረት ስራ ላይ የተሰማሩ የዳንግሽታ ቀበሌ ነዋሪዎችን በኢንስቲትዪቱ ሜከርስፔስ በማምጣት ስልጠና ተሰትዋል። በዚህ ፕሮጀክት የተሰሩ የፈጠራ ውጤቶችን አስራ ሁለት የበቆሎ መፈልፈያ እና ሶስት የብረት ጎተራ(ሲሎ) በዳንግሽታ ቀበሌ ለሚገኙ ሴት ገበሬ እራስ አገዝ ማህበራት በ እየሩሳሌም የህጻናት እና የማህበረሰብ ልማት ድርጅት አስተባባሪነት አስረክቧል። በፕሮግራሙ ላይ የ እየሩሳሌም የህጻናት እና የማህበረሰብ ልማት ድርጅት የባህር ዳር አካባቢ ማህረበሰብ ልማት ማናጀር አቶ እደግልኝ ፈንታ የባህርዳር ዩኒቨርስቲን ለተሰራው ስራ አመስግነው፤ ይህ እርዳታ ሳይሆን አርሶ አደሮች ጥቅሙን አይተው ከስለጠኑ ባለሞያዎች ጋር በመነጋገር ተጨማሪ ለማሰራት እንዲችሉ የሚያስችል መሆኑን በመግለፅ ዩንቨርሲቲውን አድንቀዋል። በቢቴክ የሜከርስፔስ አስተባባሪ ወ/ሪት ቤዛወርቅ ጥላሁን በዚህ ፕሮጀችት ተሳታፊ የሆኑትን መምህራን እውቀታቸውን እና ጊዜያቸውን ሳይሰስቱ በማካፈላቸው ምስጋና በማቅረብ፤ የሴት ገበሬዎች ማህበር አደረጃጀት መኖሩ ለ ግልጽ እና ቀላል አሰራር አመቺ መሆኑን ገልጸው የግብርና እቃዎችን ለማህበሩ ተወካዮች የቀበሌው ሃላፊ በተገኙበት አስረክበዋል።
 
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
Share