የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም ያበለፀጋቸዉን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች አስመረቀ

----------------------------------------------------------- በ2012 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ ዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ጽ/ቤት ድጋፍ የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ታስበዉ በመምህራን እና ተማሪዎች የተሰሩ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በ2/12/2012 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ ስርዓቱም የአብክመ ትምህርት ቢሮ፣ የአብክመ ቴክኒክ እና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ቢሮ፣ የአማራ ልማት ማህበር (አልማ)፣ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸዉ አካላት ተገኝተዋል፡፡ በፕሮግራሙም በ2012 በጀት ዓመት ከተከናዎኑ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ዉስጥ ትምህርት ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት ያላቸዉ የሚከተሉት ስራዎች ለታዳሚዎች ቀርበዋል፡፡ • Student Information Management System (SIMS) for Preparatory and Secondary School • Smart School Set up • Low Cost Housing by using Straw Stabilized Mud blocks for rural areas • College finder mobile application • Production of vegetables by vertical farming system for urban community • Fast digital verification system on customers laptop property በመጨሻም የፕሮግሙ ተሳታፊዎች ኢንስቲትዩቱ እያከናዎነ ያለዉን ማህበረሰብ ተኮር ተግባራት አበረታተዉ ለወደፊቱም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እና አብሮ ለመስራት ፍላጎቱ እንዳላቸዉ ገልፀዋል፡፡
images: 
Share