BiT Snapshot

የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በክቡር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር አህመዲን መሀመድ ከተመራው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ቡድን ጋር የምክክር መርሀ-ግብር አካሄደ፡፡

Body: 
ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር የዲጂታል 2025 ቡድን ጋር በ 24/04/13 ዓ.ም. የተካሄደውን የምክክር መርሀ-ግብር የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ አስተዋውቀው የከፈቱ ሲሆን የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አክለውም በአገርአቀፍ ደረጃ ትልቅ ቦታ በተሰጠው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚንስቴር ዐብይ ተግባራትን እያከናወኑ እንደመሆናቸው በሁለቱ መካከል ከሚደረጉ የምክክር መርሀ-ግብሮች ወሳኝነት ባሻገር በተግባር የተደገፈ ቅንጅታዊ አሰራር ሊኖር እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
images: 
Share