በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ማህበረሰብ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ

Body: 

በባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስርና የማህበረሰብ አገልግሎት ቢሮ ሐምሌ 02/2013 ዓ.ም. ባዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ እና የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር መኳንንት አገኘሁን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች፣ መምህራንና ተመራማሪወች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ሁሉም የተዘጋጁ ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ አሻራቸውን ማሳረፍ ችለዋል፡፡ ችግኞች የተተከሉበት ቦታ ታንታ ላጉና ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ በሚገኝ ኮረብታማ ቦታ ሲሆን በዕለቱ ከ2000 በላይ ችግኞች መተከላቸውን የቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪው አቶ ናቃቸው አሰፋ አስታውቀዋል፡፡

Share