በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የህፃናት ማቆያ ማዕከል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለሕፃናቱ ፕሮግራም አዘጋጀ

Body: 

ማዕከሉ የአዲስ ዓመት ዋዜማን ምክንያት በማድረግ ለሕፃናቱ የእንኳን አደረሳችሁ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡ ስራዉን ከጀመረ ከ3 ዓመት በላይ ያስቆጠረው ማቆያ ማዕከሉ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በማዕከሉ ተጠቃሚ የነበሩና በመጠቀም ላይ ያሉ ሕፃናትና ወላጆቻቸው የተገኙ ሲሆን የተዘጋጀላቸውን ኬክም ቆርሰዋል፡፡ የህፃናት ማቆያው ለህፃናቱ ምቹና ደረጃውን የጠበቀ መዋያ ከመሆን ባለፈ ለሴት ሠራተኞች ሃሳብና እንግልትን በመቀነስ ለተቋሙ ያላቸውን ሚና ከፍ እንደሚያደርገው ይታመናል፡፡ ማዕከሉ ከ6 ወር እስከ 3 ዓመት እድሜ ያላቸውን ሕፃናት የሚያስተናግድ ሲሆን ለመጭው አዲስ ዓመትም የኢንስቲትዩቱን ሴት የአስተዳደር ሰራተኞችና መምሕራን ልጆች ተቀብሎ ለማዋል ምዝገባ አከናውኗል፡፡
 

Share