በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የእውቅና እና የማበረታቻ መስጫ መመዘኛ መስፈርት ላይ ውይይት አደረገ


===================
ዛሬ ጥቅምት 02/2014 ዓ/ም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለትጉህ መምህራን፤ የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳት ባለሙያዎች፣ የፋኩልቲ ዲኖች እና የቼር ሆልደሮች የእውቅና እና የማበረታቻ መስጫ መመዘኛ መስፈርት አዘጋጅቶ ከተቋሙ መምህራን እና የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳት ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርጓል። በውይይቱ ላይ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት ሳ/ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ የተገኙ ሲሆን ም/ሳ/ዳይሬክተር ዶ/ር ደምስ አልማው መመዘኛ መስፈርቱን ላዘጋጁት የኮሚቴ አባላት ምስጋና አቅርበው ጠንካራ ሰራተኛን እውቅና መስጠትና ማበረታታት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ለተወያዮቹ ገልጸዋል፡፡ በመቀጠልም የእውቅና እና የማበረታቻ መስጫ መመዘኛ መስፈርት አዘጋጅ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አበራ አስቻለው እውቅና ለማግኘት እና ተሸላሚ ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን እና የመመዘኛ ነጥብ አሰጣጥ ሂደቶችን አቅርበዋል። ውይይቱንም የኢንስቲትዩቱ የአካዳሚክ ም/ሳ/ዳይሬክተር ዶ/ር ደምስ አልማው መርተዋል። ተሳታፊዎችም የቀረበውን የእውቅና እና የማበረታቻ መስጫ መመዘኛ መስፈርት ላዘጋጀው ኮሚቴ እና ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ምስጋና አቅርበው በቀረበው ሰነድ ላይም አስተያየቶች እና ጥያቄዎችን ሰንዝረዋል። በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች ኮሚቴው መልስ ከሰጠባቸው በኋላ ዶ/ር ደምስ የማጠቃለያ ሃሳብ ሰጥተው ውይይቱ ተጠናቋል።
 

Share