በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሙያ ማጎልበቻ ማዕከል የአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ እቅድ ላይ ውይይት አደረገ

=======================
ዛሬ ጥቅምት 04/2014 ዓ.ም የማዕከሉ አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ አለማየሁ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የሙያ ማጎልበቻ ማዕከሉ በዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስር ሁኖ በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን እንደቆየ በመጥቀስ የአምስት ዓመቱን ስትራቴጂካዊ እቅድ ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው እቅድ ላይም ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ በውይይቱም ላይ የኢንስቲትዩቱ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር መኳንንት ኣገኘሁ የማዕከሉ ሰራተኞችን የነቃ ተሳትፎ አመስግነው ወደፊት ማዕከሉ እቅዱን ከግብ ለማድረስ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ባንተላይ ስንታየሁ በበኩላቸው ማዕከሉ ስትራቴጂካዊ እቅዱን የሚለካበት መስፈርት እንዲኖረው በተለይም ደግሞ ስራ እና ሰራተኛን ማገናኘት፤ ስራ አጥ ምሩቃንን ከተቋሙ ተመርቀው ጥሩ ደረጃ የደረሱ ሰዎችን በመጋበዝ ልምድ እንዲቀስሙ ማድረግ እና ሌሎች ሰፊ ስራዎችን እንዲሰሩ አመላክተዋል፡፡ በመጨረሻም አቶ ሃብታሙ ለተሰጣቸው አስተያየት ምስጋናን አቅርበውና ለጥያቄዎች መልስ ሰጥተው ፕሮግራሙ ተጠናቅቋል፡፡
 

Share