ዶ/ር ካሰኝ ተክለጻዲቅ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተገኝተው የማነቃቂያ ንግግር አደረጉ


======================
ታኅሣሥ 15, 2014 ዓ.ም ዶ/ር ካሰኝ ተክለጻዲቅ ከባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማህበረሰብ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኙት ዶ/ር ካሰኝ የ2ኛ እና የ3ኛ ድግሪ ትምህርታቸውን ደግሞ ስኮትላንድ በሚገኘው ስትራትክሊድ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለዋል፡፡ በቅድሚያም ዶ/ር ካሰኝ ስለህይወት ተሞክሯቸው፣ በኢንዱስትሪ ውስጥ ስላከናወኗቸው ስራዎች ካብራሩ በኋላ በአለም ላይ ካሉ ታላላቅ የምርምር እና ስመ ጥር ካምፓኒዎች ጋር ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ችግር ፈች ስራዎችን መስራታቸውንና ከ30 በላይ የፓተንት ባለቤት መሆናቸውን አውስተዋል፡፡ ዶ/ር ካሰኝ በገለጻቸው ስለሪቨርስ ኢንጂነሪንግ፣ ጥናትና ምርምር፣ ተገቢ ቴክኖሎጂ፣ የእውቀት ሽግግር፣ ዲስራፕቲቭ ቴክኖሎጂ እና ሌሎችንም ሃሳቦች አንስተዋል፡፡ ከላይ በተነሱት ርዕሰ ጉዳዮች ላይም ከተሳታፊዎች ጋር በሀገራዊ ጠቀሜታቸው አንጻር ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ቀደም ብልውም የኤሌክትሪካልና ኮምፒዩተር ምህንድስና ፋኩልቲ መምህራንን አግኝተው ያወያዩ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ተሞክሯቸውን አካፍለዋቸዋል፡፡ በመጨረሻም ዶ/ር ካሰኝ በኢንፎርሜሽና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት የተዘጋጀላቸውን ስጦታ በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተስፋየ ሽፈራው አማካኝነት ተበርክቶላቸዋል፡፡

 

Share