በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ

Body: 
ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2014 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ በማታው መርሃ ግብር አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር በመፈለጉ ሲመዘግብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ እና ምዝገባው ያመለጣችሁ አመልካቾች ከሚያዚያ 20/2014 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 28/2014 ድረስ ባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሪጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኘት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት የሚሰጥባቸው የትምህርት መስኮች
Mechanical and Industrial Engineering Faculty
 • Mechanical Engineering 
 • Automotive Engineering
 • Electromechanical Engineering
 • Industrial Engineering
Computing
 • Information Technology
 • Computer Science
 • Software Engineering
Civil and Water Resource Engineering
 • Civil Engineering
 • Hydraulic and Water Resource Engineering
 • Water Resource and Irrigation Engineering
Electrical and Computer Engineering
 • Electrical Engineering
 • Computer Engineering
Chemical and Food Engineering
 • Applied Human Nutrition
የመግቢያ መስፈርት፡-
1. የመሰናዶ ትመህርት ለጨረሱ
 • በትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርት መሰረት
2. ዲፕሎማ ላጠናቀቁ
 • ከ1994 ዓ.ም በፊት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በዲፕሎማ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ እና ከ1994 ዓ.ም በኋላ ከየትኛውም ተቋም ትምህርታቸውን በ10+3 ወይም በደረጃ-4 ያጠናቀቁ እና የደረጃ-4 የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የሚያቀርቡ
ማሳሰቢያ፣
 • በድሮውም ሆነ በደረጃ-4 ዲፖሎማ ለምትመዘገቡ ኦፊሻል ትራንክሪፕት ከምዝገባ በፊት መድረስ አለበት 
 • የትምህርት ማስረጃ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ እንዲሁም
 • ለማመልከቻ 100 ብር መክፈል ይጠበቅባችኋል
የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሪጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት
Date: 
Friday, April 29, 2022 - 15