የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከል አካዳሚያዊ ጽሁፎች እና ህትመቶችን በተመለከተ ሥልጠና መሥጠት ጀመረ

በኢንስቲትዩቱ ውስጥ የሚጻፉ አካዳሚያዊ ጽሁፎች እና ሕትመቶችን ጥራት እና ብዛት ለማሳደግ ያለመ ሥልጠና ለኢንስቲትዩቱ መምህራን በELIC አማካኝነት መሥጠት ተጀመረ። በተባባሪ ፕሮፈሰር ዳዊት አሞኘ እና ዶ/ር አማረ ተስፋዬ የሚሠጠው ሥልጠናው ከአካዳሚያዊ ጽሁፎችን ጽንሰ ሐሳብ ጀምሮ ለሕትመት እንዴት መጻፍ እንደሚገባም ገንዛቤ እንደሚያስጨብጥ ይጠበቃል። ሥልጠናው ለ2 ቀን የሚቆይ ሲሆን ጽሁፎችን ማረም እና ማስተካከል የሚቻለበትን መንገድ ጨምሮ የምርምር ህትመት ሥነ መዋቀር እና ከህትመቱ ጋር ተያይዞ ሊታወቁ የሚገቡ ተኣማኒነት ያላቸውን አሳታሚ ጆርናሎችን ብሎም በሕትመቱ ወቅት ሊገጥሙ የሚችሉ ፈተናዎችን እና የግምገማ ሂደቱን በተመለክተ ግንዛቤ እንደሚያስጨብጥ ይጠበቃል።
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
Share