በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለባሕር ዳር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መምሕራን ስለ Action Research ሥልጠና ሰጠ።

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስርና የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በባሕር ዳር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት Action Research ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ የባሕር ዳር ፖሊቴክኒክ መምሕራን የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናውን የመሩት ዶ/ር አማረ ተስፋዬ እና ዶ/ር ብርሐኑ አስረስ ሲሆኑ ለ1 ቀን በቆየው ሥልጠና በጠዋቱ ፕሮግራም Action Research ጋር በተያያዘ ከምንነቱ በመነሳት ባህሪያቱን ጨምሮ ከBasic Research የሚለይበትን መንገድ በንድፈ ሐሳብ ደረጃ ለተሳታፊ መምሕራን ተብራርቷል። በከሰዓቱ ፕሮግራም ችግሮችን መለየት፣ አማራጭ የመፍትሄ መንገዶችን መንደፍ ጨምሮ ተግባራዊ እንዲሆን በማሰብ ፕሮፖዛል ማዘጋጀትን የሚጨምር ሥልጠና ተሰጥቷል።
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
Share