የዘላቂ ኃይል ልማት ለገጠር ሥራ ፈጥራ ፕሮጀችት ምረቃ በዳንግላ ወረዳ ዳንጊሽታ ቀበሌ ተካሄደ

በጀርመኑ Technical University of Munich በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በትብብር የተገነባው በታዳሽ ኃይል የመስኖ ልማት እና ኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ሥራ መጀመሩን አስመልክቶ  የፕሮጀክቱ ምረቃ ተካሄደ። በፕሮግራሙ መክፈቻ ወቅት የፕሮጀክቱ መሪ ዶ/ር ንጉስ ጋብየ እደተናገሩት ዘመናዊ እና ታዳሽ  ኃይል ከማመንጨት ባለፈ ወጣቶችን በትናንሽ የማኑፋክቸሪንግ ሥራ ዘርፍ እንዲሰማሩ እድል ይፍጥራል። እንደ እሳቸው ገለጻ 160 ሜትር ጥልቅ ጉድጓድ ተቆፍሮ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ ፓምፕ ተግጥሞለት ለመስኖ ግልጋሎት ውሏል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ለአርሶ አደሮች አጭር ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን በጠብታ መስኖ እስከ 10 ሄክታር  መሬትን ማልማት የሚችል እና 1800 አባውራዎችን የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ያደርጋል። ለዚህም ሥራ የሚሆን ገንዘብ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 4 ሚሊዮን ብር የተለገሰ ሲሆን ወጣቶችን አደራጅቶ ወደ ሥራ ከመሰማራት ባለፈ ምርምር ለሚያደርጉ የድሕረ መረቃ ተማሪዎች እንደ Living Lab ሆኖ የሚያገልገግል ስፍራ ነው። በእለቱ የተገኙት የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ የቀበሌው ነዋሪዎችን እና ባለ ድርሻ አካላትን አመስግነው  ሥራው ከ2007 ዓም ጀመሮ በምርምር ሂደት ላይ እንደነበር ብሎም ከ15 የሚበልጡ የድሕረ ምረቃ ተማሪዎች እድሉን እንዳገኙ ገልጸዋል። የሲቪል እና ውሐ ሐብት ምህንድስና መምሕር እና የፕሮጀክቱ ተሳታፊ የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ በበኩልቸው የሕብረተሰቡን ቁርጠኝነት አድንቀው በአሁኑ ወቅት 10000ሊትር የሚይዝ የውሃ ታንከር ተተክሎ ለሕበረተሰቡ ንፁህ የባንቧ ውሃ በተመረጡ ቦታዎች መቀመጡን ገልጸው አርሶ አደሮችን ትጋት አድንቀዋል። 
የቀበሌው ነዋሪ እና በህልውናው ጦርነት ተሳታፊ የነበሩት ሚሊሻ ውባንተ እያሱ የዶ/ር ንጉስ ጋብዬን ሐሳብ በመጋራት ለወጣቶች የጸጉር ቤት ሥራ ጀመሮ እንጨት መሠንጠቂያ ቤቶችን ለመሥራት በዕቅድ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። እንደ ሚሊሻ ውባንተ ንግግር በአሁኑ ወቅት 28 አባውራዎች የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ሆነው የመስኖ ድንች ያለሙ ሲሆን በቀጣይ ሌሎች ለመቀላቀል በሂደት ላይ መሆናቸውን ለማየት ተችሏል። በዚህ ወቅት ካነጋገርናቸው አርሶአደሮች ውስጥ ጥቂቶቹ የባሕር ዛፍ ደኖቻቸውን በመመንጠር ላይ መሆናቸውን ገልጸው በ 5 ዓመት የሚያገኙት የባሕር ዛፍ ትርፍ ከመስኖው ዝቅተኛ መሆኑን በመግለጽ ወደ መስኖው ለመግባት በሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። 
በኣጠቃላይ በፀሐይ ኃይል ይሚሰራው ታዳሽ ኃይል እስከ 25 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጨ ሲሆን 30ሊትር በሰከንድ የሚሆን ውሃ ከጉድጓዶቹ መውጣት መቻሉን ዩኒቨርሲቲው መምህር እና የፕሮጀክቱ ተሳታፊ አቶ ነገሰ ያዩ ገልጸዋል። ቁፋሮው በአማራ ውሓ ስራዎች የተከናወነ መሆኑን በመጠቆም የአማራ ክልል ውሐ እና ኢነርጂ ቢሮ ጥናት በማካሄድ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳበረከተ አቶ ነገሰ ገልጸዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ጉዳዮች ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ገደፋው አላግባብ ብክነት እና ጥፋት እንዳይኖር መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸው በሞዴል ደረጃ የሆንው ስራውን በማስፋፋት ወደሌሎች ቦታዎች ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል። በሌላ በኩል ለመዝረፍ የሚፈልጉ ኃይሎች እንደመኖራቸው መጠን ቀን ከለሊት ክትትል እንደሚያስፈልገው በገልጻቸው ወቅት አብራርተዋል። በተጨማሪም የአዊ ዞን፣ የዳንግላ ወረዳ እና የዳንግሽታ ቀበሌ አመራሮች በየደረጃቸው አስተያየታቸውን ገልጸዋል። 
በመጨረሻም ለፕሮጀክቱ እዚህ መድረስ ከፍትኛ ሚና ነበራቸው የተባሉ ግለሰቦችን እውቅና የመስጠት መርህ ግብር ተካሂዶ  የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል።  
 
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
                     
Share