በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለተከታታይ 20 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የግንባታ መረጃ ሞዴሊንግ (BIM) ሥልጠና ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አማካኝት በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ውስጥ ሲካሄድ የነበረው የ20 ቀን ስልጠና ተጠናቀቀ። በወቅቱ ስልጠናው መጠናቀቁን አስመልክቶ ለሠልጣኞች በኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢምረው ታምራት አማካኝነት ሰርቴፍኬት የተበረከተ ሲሆን የሲቪል እና ወሃ ሃብት ምህንድስና ፋኩልቲ ዲን ዶ/ር ምትኩ ዳምጤ የኢትዮጵያ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩቱን አመስግነዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አመራር የሆኑት እጩ ዶክተር ዘሓራ አብዱልሃዲ ሰልጣኞች የግንባታ መረጃ ሞዴሊንግ አምባሳደሮች መሆናቸውን ጠቁመው ከካሪኩለም ቀረጻ ጀምሮ ለተማሪዎች እና በጊቢው ለሚገኙ መምህራን ተከታታይ ሥልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህም ጋር ተያይተው በሌሎች መስክ የሚታየውን ዲጂታል ሥርዓት በግንባታው ዘርፍም ዲጂታዊ አሰራርን ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። 
በሌላ በኩል የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አካዳሚክ ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ደምሰው አልማው የሠርተፍኬቱ ዋጋ ትልቅ መሆኑን ጠቁመው ሥልጠናውን ያዘጋጀውን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩትን አመስግነዋል። እያንዳንዱ ሠልጣኝ ኃላፊነት እንዳለበት ጠቁመው ሐገርን ለማሳደግ መተባበር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። 
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
 
   
   
Share