በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች የዲፓርትመንት ምርጫ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ

በኢንስቲትዩቱ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ በለጠ መርሻ የተከፈተው ዝግጅት በተቋሙ የሚሰጡትን የትምሕርት መስኮች በተመለከተ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠበት ሲሆን ተማሪዎች የሚመርጧቸው የትምህርት መስኮች በዕውቀት እና ገንዛቤ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያስችላቸዋል ተብሏል። በዝግጅቱ ሁሉም የኢንስቲትዩቱ የትምህርት መስኮች በውስጣቸው የሚሰጡ ፕሮግራሞችን እና ተማሪዎቹ የሚኖራቸውን እድሎች ያስገነዘቡ ሲሆን  በቀጣይ የተማሪዎች የትምህርት መስክ ምርጫ ከግንቦት 26 እስከ 28 እንደሚካሄድ ተገልጿል።  
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
Share