በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለ42 አመታት በመምሕርነት እና በአምራርነት ያገልገሉት ተባባሪ ፕሮፌሰር ንጉሴ ሙሉጌታ የሽኝት መርሐ ግብር በሜካኒካል እና ኢንዱስቲሪያል ፋኩልቲ አዘጋጅነት ተካሄደ

 
በፋኩልቲው ውስጥ የሚገኙ መምህራን እና ሠራተኞች ባዘጋጁት ምርሐ ግብር ወቅት እንደቀረበው ተባባሪ ፕሮፌሰር ንጉሴ ሙሉጌታ ለ42 አመታት ዩኒቨርሲቲውን በተለያየ አመራርነት ቦታ እና መምሕርነት ያገለገሉ ሲሆን የማስተርስ እና የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከሩሲያ አግኝተዋል። አባትነት፣ ተጫዋችነት፣ ተግባቢነት እና ፈጣን ውሳኔ ሰጭነታቸውን የቀድሞ ተማሪዎቻቸው እና የፋኩልቲው ማሕበረሰብ አባላት የገለጹ ሲሆን የሕይወት ታሪካቸውን አስተማሪ እንደሆነም በመድረኩ ተገልጿል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ተባባሪ ፕሮፌሰር ንጉሴ ሙሉጌታ በኢንስቲትዩቱ ቢሻሻሉ የሚሏልቸውን ጉዳዮች በጠቆሙበት ፕሮግራም የፋኩልቲው አባላት ምስጋናቸውን በሽልማት እንደገለጹላቸው ለማወቅ ተችሏል። በሌላ በኩል በሕልውና ዘመቻው ወቅት ከሚጠበቅባቸው በላይ በማገልግል ፋኩልቲውን በመልካም ሥራ ያስጠሩ የፋኩልቲው አባላት ሽልማት አሠጣጥ የተካሄደ ሲሆን ክዚህም ጋር ተያይዞ በፋኩልቲው በሚገኙ የትምሕርት መስኮች ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሠርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። 
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
Share