በባሕር ዳር ዙሪያ ለሚገኙ የዘይት እና ዱቄት አምራች ፋብሪካዎች በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሥልጠና ተሰጠ

ሥልጠናው ለሦስት ተከታታይ ቀናት የቆየ ሲሆን ጥራት እና ምርታማነት ለማሳደግ ያለመ መሆኑን በመዝጊያው ወቅት ተገልጿል። ሥልጠናው በዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት እና በኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ የተዘጋጀ እና ከንድፈ ሐሳብ ጀምሮ ተግባር ተኮር ትምህርቶችን ለመሥጠት እንደተቻለ ለማወቅ ተችሏል። በሥልጠናው መዝጊያ ወቅት ከሰልጣኞች የጊዜ እጥረት፣ ተግባራዊነት፣ አመለካከት ብሎም አስገዳጅነትን በተመለከተ ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ከመምሪያው የተገኙት አቶ አቤል መሳይ ፋብሪካ ተኮር የሆኑ ሥልጠናዎች እንደሚቀጥሉ በመግለጽ በያንዳንዱ ዘርፍ የሚገኝ ተቋም እና አመራር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።  
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
Share