በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ስልጠና ተሰጠ

በስልጠናው  ዶ/ር አማረ ተስፋዬ፣ የማዕከሉ ዳይሬክተር እንደገለፁት ከሆነ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ስልጠና በዋናነት የአካድሚክ ጽህፋ እና ህትመት ላይ ያተከረ እንደሆነ አና የተማሪዎችን የመፃፍ ክህሎት ለማዳበር የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ ገልፃዎል፡፡ ዳይሬክተሩ አያይዘውም ክ 50 እስከ 60 በመቶ የሚሆኑት የአካዳሚክ ጽሑፎች ከጅምሩ በዴስክ ደረጃ የሚቀሩ ሲሆን የሕትመት ጥራት ውስጥ ቋንቋ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ መድረኩን የከፈቱት የኢንስቲትዩት የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ደምሰው ዓልማው ሴንተሩ መምሕራን እና ተማሪዎችን ለማገዝ እንደተቁቋመ ገልጸው፤የአካዳሚክ ሕትመት ወረቀት የራሱ ጥበብ እንዳለው የጠቆሙት ዶ/ር ደምሰው ግርታን ከማጥራት ባለፈ ፀሐፊያን ሁሌም የሚቸገሩበትን የቋንቋ ጉዳይ ለመፍታት ሥልጠናው ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ጠቁመዋል። ሥልጠናው በተባባሪ ፕሮፌሰር ዳዊት አሞኘ እና ሙሉጌታ አድማሱ አማካኝነት የተሰጠ ሆኖ ለሁለት ተከታታይ ቀናት መቆየቱን ለማወቅ ተችሏል።  
ከዚህም በተጨማሪ ማዕከሉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለማሻሻል ለአንድ ወር የሚቆይ ስልጠና የተጀመረ ሲሆን፣ በስልጠናው የተማሪዎችን  ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉ ርዕሶች ተካትተውበታል፡፡
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
Share