የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ

የዲሞክራሲ ሥራዓት ግንባታ ማዕከል ሚኒስትር እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ ሌሎች የቦርዱ አባላት የተገኙበትን የጉብኝት ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኝ እና የኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢምረው ታምራት መርተዋል:: በጉብኝቱም ግንባታዎችን ጨምሮ በግቢው ውስጥ እየተከናውኑ ያሉ ሌሎች ሥራዎች የተመለከቱ ሲሆን በቢዝነስ ኢንኩቤሽንና ቴክኖሎጂ ስራ ፈጠራ ማዕከል (BiTec) የተሰሩ የተማሪዎችና መምህራን ፕሮጀክቶችም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል:: ማዕከሉን ጎብኝተው ሲጨርሱም ለቦርዱ አባላት የBiTec እና የSeifu BiT Makerspaceን አርማ የያዙ የተለያዩ ስጦታዎች ተበርክቶላቸዋል:: በመቀጠልም Jan-Moscov ቤተ መፅሐፍትን የጎበኙ ሲሆን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አሠራርን በመዘርጋት ብዙ ተማሪዎችን ለማገልገል ያለመ መሆኑ ተብራርቷል። በተጨማሪም በአሁኑ ሰዓት በውስጡ ከ80 እስከ 90 ሺ የሚሆኑ መፅሐፍት ያሉት ዘመናዊ ቤተ መፅሐፍት መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል። ከዚህ ጋርም ተያይዞ BAHIR DAR STEM INCUBATION CENTER የጎበኙ ሲሆን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፓርክ ለመሥራት በሐሳብ ደረጃ የተቀመጠ መሆኑ ተጠቁሟል። ዘመናዊ እና የተሟላ ቤተ ሙከራ የተካተተበት ሴንተሩ ተማሪዎቹ በእጆቻቸው እየነካኩ ትምህርት የሚቀስሙበት መንገድ መፈጠሩ ክህሎታቸውን ኢንዲያዳብሩ መንገድ እንደሚከፍት በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል። ከጉብኝቱ በሗላም የሥራ አመራር ቦርዱ በፕሬዝደንት ጽቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ እስከነገ ቆይታ ይኖረዋል የተባለውን መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል:: የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ፌስቡክ፡- Bahir Dar Institute of Technology, Bahir Dar University, Ethiopia ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et

Share