ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

Body: 

ቀን፡ 23/10/2014 ዓ.ም

ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲየባሕር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮች እና አስተዳዳሪዎች ለመምረጥና ለመሰየምነሃሴ/2013ዓ.ም የወጣውንመመሪያቁጥር 01/2021መሰረት በማድረግ የባሕርዳርዩኒቨርሲቲ ለባሕር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የማኔጂንግ ዳይሬክተር የኃላፊነትቦታ ላይ ማገልገል የሚችሉ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመመደብይፈልጋል፡፡

የመወዳደሪያ መስፈርት፡-

1ኛ. የትምህርት ደረጃ በምህንድስና፣ በቴክኖሎጅ ፤ በሳይንስ ወይም በማኔጅመንት እና ከማኔጅመንት ጋር በተቀራረበ የትምህርት ዘርፍ ሌክቸረር እና ከዚያ በላይ የሆነ/የሆነች፤"

2ኛ. የስራ እና የአመራርነት ልምድ፡-

ሀ/ ከመጀመሪያ ዲግሪ በኋላ 6 ዓመትና ከዚያ ላይ ልምድ ያለው/ያላት፣

ለ/ ሶስተኛ ዲግሪ ያለዉ/ያላት እና በዲፓርትመንት ሃለፊ ደረጃ እና ከዚያ በላይ በሆነ አመራርነት 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ ያገለገለ/ያገለገለች ወይም ሁለተኛ ዲግሪ ያለዉ/ያላት እና በዲፓርትመንት ሃለፊ እና ከዚያ በላይ በሆነ አመራርነት      5 አመት እና ከዚያ በላይ ያገለገለ/ያገለገለች፤

3ኛ. የተቋሙን ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እና ግብ ለማሳካት የሚያስችል ስልታዊ እቅድ (Strategic Plan) ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፤

4ኛ. ከማንኛዉም አይነትየዩኒቨርስቲ/የተቋም ፈቃድ ውጭ የሆነ/የሆነች፤

      መሟላት ያለባቸው ሰነዶች፤

1.   ማመልከቻ ደብዳቤ፣

2.   የግለ ታሪክ መግለጫ (CV)፣

3.   የትምህርት ማስረጃ ኮፒ፣

4.   ከሰዉ ሃይል አስተዳድር የተረጋገጠ  የስራና የአመራርነትልምድ፣

5.   ስልታዊ እቅድ (Strategic Plan) (ከአምስት ገጽ ያልበለጠ)

አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ማለትም ከ23/10/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሼን ጽ/ቤት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ አካል ጉዳተኛ አመልካቾች ከሚመለከተዉ አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፤

ለበለጠ መረጃ በሚከተለው ስልክ ቁጥር በ0911901055 ደውለው ማነጋገር ወይም የተቋሙን ድረ-ገጽ bdu.edu.et እና bit.bdu.edu.et መመልከት ይችላሉ፡፡

  በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዕጩ አፈላላጊና አስመራጭ ኮሚቴ

Date: 
Thursday, June 30, 2022 - 10