የBiT የጤና እግር ኳስ ቡድን 2ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅና 3ቱንም ከዋክብት በማስመረጥ ድንቅ ብቃቱን አስመስክሯል

 
ዛሬ በተካሄደው የባህር ዳር ከተማ የጤና ቡድኖች የፍጻሜ የእግር ኳስ ጨዋታ የBiT እና የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ቡድኖች የተገናኙ ሲሆን በመደበኛው 90 ደቂቃ 2-2 አቻ ተለያይተው በመለያ ምት ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጤና ቡድን የBiT የጤና ቡድንን 4-3 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት መሆን ችሏል::
 
የBiT የእግር ኳስ ቡድን ምንም እንኳን ዋንጫ ባይቀናውም 3ቱንም የውድድሩ ከዋክብት በማስመረጥ የተመልካችን አድናቆት ተችሯል:: የቡድኑ አምበል ሃይለየሱስ ሙሏለም 20 ጎሎችን በማስቆጠር የውድድሩ ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ ከማጠናቀቁ ባሻገር ባሳየው ድንቅ ብቃት የውድድሩ ኮከብ ተጨዋች በመሆን ተመርጧል:: በሌላ በኩል የቡድኑ ግብ ጠባቂ ፈንታሁን ክንዴም የውድድሩ ኮከብ በረኛ በመሆን ተመርጧል::
 
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጅክ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬትም በከዋክብቱ መመረጥና ቡድኑ ባስመዘገበው ድንቅ ውጤት የተሰማውን ኩራት እየገለጸ ለኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብና ለቡድኑ ደጋፊዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክቱን ያስተላልፋል::
የዋንጫው ባለቤት ለሆነው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ቡድንም እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን::
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
 
ፌስቡክ፡- Bahir Dar Institute of Technology, Bahir Dar University, Ethiopia
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
Share