የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን ሥምምነት ተፈራረመ።

[መስከረም 16፣ 2015 ዓ.ም ባሕር ዳር፣ ኢስኮ/ባቴኢ]
**************************
በመክፈቻው ወቅት የዩኒቨርሲቲው የኢንፎርሜሽን እና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ዘውዱ እምሩ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው 60ኛ ዓመቱን ለማክበር በመንደርደር ላይ መሆኑን ገልጸው ባሕር ዳር ከተማን የዩኒቨርሲቲ ከተማ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ አብራርተዋል። በ15 የአካዳሚክ ክፍሎች የተዋቀረው የኒቨርሲቲው በተለያዩ የምርምር ማዕከላት እና የላቀ የትምሕርት ጥራት በሐገር አቀፍ ደረጃ ምርጥ የምርምር ዩኒቨርሲቲ መባሉን አውስተዋል። 
የዩኒቨርሲቲው ፕረዝደንት ዶ/ር ፍሬው ተገኝ በበኲላቸው ለሐገር አዳዲስ የትምሕርት ዘፎችን በማስተዋወቅ ቀዳሚ የሆነው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአማራ ክልል በሚከናወኑ የውሃ መሥኖና ኢነርጂ ሥራዎች ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ በመግለጽ ስምምነቱ ለሐገር የሚኖረውን ፋይዳ አውስተዋል። ይሕንን ሓሳብ በመደገፍ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢምረው ታምራት ኢንስቲትዩቱ ያለውን እምቅ የሰው ኃይል በመጠቀም ተባብሮ መሥራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። 
የኢትዮጵያ ኤሊክትሪክ ኃይል  ኮሮፕሬት ፕላኒንግ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም ሲያ በበኩላቸው እየተሰሩ ያሉ ምርምሮች ከውጪ አማካሪዎች ጋር እንደመሆናቸው መጠን ከዩኒቨርሲቲው ጋር የሚኖረው ሥምምነት ይህንን ለማስቀረት ጥቅሙ የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል። በሌላ በኩል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እንደመሥራታቸው መጠን በምርምር እና የተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመተባበር ሕብረተሰቡን የሚጠቀም ሥራ ለመስራት እንደሚያስችል ጠቁመዋል። በመጨረሻም የኤለክትሪካል እና ኮምፒውተር ምሕንድስና ፋኩልቲ ዲን አቶ ቲዎድሮስ ጌራ በኢትዮጵያ ደረጃ የመጀመርያ የሆኑት አዳዳስ ፕሮግራሞች ውስጥ በመሳተፍ የተሻለ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። 
Information and Strategic Communication Directorate
 
 
               
Share