Submitted by hateyo on
Body:
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የመካከለኛና ዝቅተኛ አመራር ምርጫ፣ ሹመት፣ ምደባ ለመደንገግ የሴኔት መመሪያ ቁጥር 05/2014 መስፈርት መነሻ በማድረግ ለመካከለኛና ዝቅተኛ የአካዳሚክ ኃላፊነት ቦታዎች ማወዳደሪያ መስፈርት አፅድቆ እየተገበረ ይገኛል። በዚህም መሰረት ለአካዳሚክ ፕሮግራም የዳይሬክተርነት ቦታ ለመወዳደር የምትፈልጉ መምህራን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የትምህርት እና የሥራ ልምዳችሁን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ከአምስት ገፅ ያልበለጠ ስልታዊ ዕቅድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢንፎርሜሽንና ስትራቴጅክ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ማቅረብ ይኖርባችኋል።
የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
Date:
Thursday, November 3, 2022 - 11