ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

Body: 

ቀን፡ 11/4/2015 ዓ. ም

                                      ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ                       

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የመካከለኛና ዝቅተኛአመራርምርጫናአሰያየምመመሪያቁጥር 05/2014 አመራሮችን ለመሰየም በወጣ መመሪያ መሰረት በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኤሌክትሪካና ኮምፒውተር ኢንጅነሪንግ ፋኩሊቲ ዲን የሃለፊነት ቦታ  አመልካቾችን አወዳድሮ ለመሾም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የፋኩሊቲው መምህራን እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡

1.   የትምህርትደረጃ፡- የሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ በኤሌክትሪካና ኮምፒውተር ኢንጅነሪንግ የትምህርት መስክ ያለው/ያላት

2.   የፋኩሊቲውን ዓላማ ለማሳካት የሚያግዙ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግና ዋና ተግባራቱን ለማስፈፀም የሚያቀረቡት አጭር የስራ እቅድ /ንድፈ ሃሳብ/ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል

3.   የፋኩሊቲው ማህበረሰብ አባላት በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ቀርቦ/ባ ገለፃ ማድረግ እና ማብራሪያ  መስጠት የሚችል/የምትችል

4.   ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፤

አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ፡ ቀጥሎ ከተራ ቁጥር I - V የተዘረዘሩትን መረጃዎች፡

         I.     ማመልከቻ

        II.     ሲቪ (CV) 

       III.     የትምህርት ዝግጅት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ

       IV.     የስራና የአመራርነት ልምድ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ

        V.     ዋና ተግባራቱን ለማስፈፀም የሚያቀርቡት አጭር የስራ እቅድ /ንድፈ ሃሳብ/

በባሕርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኢንፎረሜሽንና ስተራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በአካል በመገኘት በተዘጋጃው የማመልከቻ መረካከቢያ ቅፅ ላይ  በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች:+251-588 209338 ደውሎ ወይም በአካል ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ማስታወቂያውን እንድሁም፡ የስራ መደቡን ተግባርና ሃላፊነት በተቋሙ ድረ ገጽ https://bit.bdu.edu.et/announcement/position/fece-dean ማግኘት ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ

አመልካቾች ዋና ተግባራቱን ለማስፈፀም የሚያቀርቡት አጭር የስራ እቅድ ፅሁፍ/ንድፈ ሃሳብ/ ከ 5 ገፅ ያልበለጠ፡ ሆኖ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚዘጋጅ ሲሆን፡ Power Geez Unicode1/Times New Roman የፅሁፍ መጠን 12 የሆነ፡ በመስመር መካከል ያለ ስፋት 1.5 የሆነና ማሪጂን/የጠርዝ ክፍተት (ከቀኝም፡ ከግራም፡ ከላይም፡ ከታችም ፡ 1 ) መሆን አለበት፡፡

Date: 
Wednesday, December 21, 2022 - 11