የባህርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2010 ዓ.ም በማታው መርሃ ግብር በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከ15/01-26/01/2010 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፡፡
ቅበላ የሚከናወንባቸው ፕሮገራሞች፡-
- Civil Engineering
- Hydraulics & Water Resource Engineering
- Computer Science
- Information Technology
- Software Engineering
- Computer Engineering
- Electrical Engineering
- Automotive Engineering
- Industrial Engineering
- Mechanical Engineering
- Electro Mechanical Engineering
- Chemical engineering
የመግቢያ መስፈርት
በትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርት
መሰናዶ ፈተና ለወሰዱ:-
- በ2009 ዓ.ም 295 እና ከዚያ በላይ
- በ2008 ዓ.ም 295 እና ከዚያ በላይ
- በ2007 ዓ.ም 275 እና ከዚያ በላይ
- በ2006 ዓ.ም 250 እና ከዚያ በላይ
- በ2005 ዓ.ም 265 እና ከዚያ በላይ
- በ2004 ዓ.ም 265 እና ከዚያ በላይ
- በ2003 ዓ.ም 265 እና ከዚያ በላይ
- በ2002 ዓ.ም 280 እና ከዚያ በላይ
- በ2001 ዓ.ም 200 እና ከዚያ በላይ
በ1995-2000 ዓ.ም የመሰናዶ ፈተና ወስደው ውጤት ያስመዘገቡ
ከ1994 ዓ.ም በፊት ዲፕሎማ ያጠናቀቁ
ከ1994 ዓ.ም በፊት ከቴ/ሙያ ኮሌጆች በዲፕሎማ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁና ከ1994 ዓ.ም በኃላ ከየትኛውም ተቋም ትምህርታቸውን በ10+3 ወይም በደረጃ 4 ያጠናቀቁ የደረጃ 4 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የሚያቀርቡ፡፡
የትምህርት ማስረጃ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ
ለማመልከቻ ብር 50.00
ማሳሰቢያ፡- በሀገር አቀፍ ደረጃ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ላልተዘጋጀላቸው የትምህርት ዘርፎች ተቋሙ የመግቢያ ፈተና ይዘጋጃል፡፡
የሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
Date:
6 Oct 2017
Place:
Bahir Dar Institute of Technology