ለሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2013 የትምህርት ዘመን አዲስ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎችን በመደበኛ መርሃ ግብር ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ https://bit.bdu.edu.et/node/592 የማመልከቻ ቅጹን በማውረድና (Download) በመሙላት ትምህርቱ ወደሚሰጥባቸው የትምህርት ክፍሎች ሬጅስትራር E-mail አድራሻ በመላክ እንድታመለክቱ እያሳሰብን፡ ሌሎች መሟላት የሚገባቸውን ዶክመንቶች፤ትምህርቱ የሚሰጥባቸውን የሙያ መስኮች እንዲሁም የትምህርት ክፍል ሬጅስትራሮችን E-mail አድራሻ ከድረ ገጻችን እንድትመለከቱ እያስታወቅን ወቅታዊውን የጤና ችግር በማስታወስ ለሁላችንም ጤና ሲባል በአካል የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን!!!

ማስታዎሻ የማመልከቻ ቅጹ፣የትምህርት ክፍሎች ሬጅስትራር አድራሻ፣የትምህርት መስኮች ሁሉም ከዚህ ማስታወቂያ ጋር ተያይዘዋል

 

Date: 
17 Sep 2020
Place: 
BiT-Bahir Dar University
Share