Call for scholarship applications

በ2013 ዓ/ም የነፃ ትምህርት ተጠቃሚ ለመሆን ለሚፈልጉ አመልካቾች

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ/ም በመደበኛ መርሃ ግብር በሚሰጡ የ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በሚኖሩት ክፍት ቦታዎች የነፃ ትምህርት እድል ለመስጠት አቅዷል፡፡ እድሉን ላገኙ እጩዎች ዩኒቨርስቲው የትምህርት ወጭዉን ብቻ (የምርምር፣ የምግብ፣ የዶርምና የህክምና አገልግሎት ወጭን ሳይጨምር) የሚሸፍን መሆኑን ይገልፃል፡፡ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

ሀ) በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት (እስከ መስከረም 30 ቀን 2013) የማመልከቻ ፎርማሊቲዎችን አሟልቶ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፤

ለ) በምዝገባ ወቅት ኢፊሺያል ትራንስክሪፕት (Official Transcript) ለሬጅስትራር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

ሐ) የመጀመሪያ ድግሪ አማካይ ውጤት ለወንዶች 3.50፣ለሴቶች፣ለአካል ጉዳተኞችና የታዳጊ ክልል አመልካቾች 3.00 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፤

መ) የመግቢያ ፈተና ወስደው ያለፉ መሆን ይኖርበቸዋል፤

ሠ) ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የስራ አጥ ማስረጃ፤

ረ) የነፃ ትምህርት ዕድል ለማግኘት ማመልከትና ለነፃ ትምህርት የተዘጋጀውን ፎርም መሙላት ይጠበቅባቸዋል::

ማስታዎሻ፦ የማመልከቻ ቅጹ፣ ከዚህ ማስታወቂያ ጋር ተያይዟል

 

Date: 
20 Sep 2020
File Attachment: 
Place: 
BiT- Bahir Dar University
Share