ለ2ኛ ድግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

***********************************************************

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በ2013 ዓ.ም በሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ የትም/ት መስኮች ከአሁን በፊት በዊክንድ መርሃ ግብር (Weekend Program) ስናስተናግድ የነበረውን በ”Online” ፕሮግራም የስልጠና መስኮች ተማሪዎችን ተቀብሎ በአዲስ አበባ ለማስተማር እስከ ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም ድረስ ማስታወዊያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የአመልካቾችን ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት የምዝገባ ጊዜውን እስከ ህዳር 20/2013 ዓ. ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፤ አመልካቾች ከዚህ በታች የተዘረዝሩትን ማስረጃዎች በ bitdistance@gmail.com ሞልታችሁ ከተቀመጠው የምዝገባ መጨረሻ ቀን በፊት ሞልታችሁ በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። 1ኛ. የመመዝገቢያ ቅጽ (Application form) 2ኛ. የባንክ ክፍያ ደረሰኝ (Bank Payment sleep) እንዲሁም “official transcript” በሚከተለው አድራሻ እንድትልኩ እናሳስባለን።
ባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ 
ፓ.ሳ.ቁ. 26 
ባህር ዳር 
ኢትዮጵያ
በተጨማሪም ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተመዝግባችሁ ክፍያ የከፈላችሁ ተማሪዎች በሙሉ በ bitdistance@gmail.com የከፈላችሁበትን የከፍያ ደረሰኝ በማማያዝ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
Date: 
9 Nov 2020
Image: 
Place: 
BiT-Bahir Dar University
Share